Monday, September 15, 2014

የእንቁጣጣሽ ስጦታ! “ክላሲካል ሙዚቃን በልምድ መጫወት አይቻልም”

  አዲስ አድማስ

የኒውዮርክ ታይምስ መጽሔት “From Chopin to Ethiopia and Part way Back Again (“ከቾፐን እስከ ኢትዮጵያ እና ደርሶ መልስ”) በሚል ባስነበበው የሙዚቃ ቅኝት ስቲቭ ስሚዝ ስለግርማ ይፍራሸዋ ያሰፈረው በከፊል ይሄን ይመስላል፡-
 “…በተነፃፃሪ ሲታይ፤ ስለክላሲካል ሙዚቃ በአፍሪካ፤ የሚያመላክቱ ጥቂት ማረጋገጫዎች ብቻ ይኑሩ እንጂ የምዕራቡ ክላሲካል ባህል በሌላው ዓለም ማለትም ከቬኔዝዌላ እስከ ቻይና እንደተንሰራፋው ሁሉ የአፍሪካንም ዙሪያ መለስ ማዳረሱ ገሀድ ነው፡፡ ለዚህ አስረጅ የሚሆነን 45 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ፒያኒስትና ቀማሪ ግርማ ይፍራሸዋ በብሩክሉንኢሹ ፕሮጀክት ሩምቅዳሜ ምሽት ያቀረበው ምርጥ የፒያኖ ሥራ፤ እጅግ ብርቅ፣ ሥነ ውበታዊና ተምሳሌታዊ የክላሲካል ሙዚቃ መናኸሪያ መሆኑን የሚያሳይ ነው!
…. ግርማየኢትዮጵያዊያን በገናሊባል በሚችለው በክራር ነው የሙዚቃ ልጅነቱን የጀመረው፡፡ አዲስ አበባ ሙዚቃ /ቤት ሲገባ ከፒያኖ ጋር ተገናኘ፡፡ ከዚያ ነው በነቃ አዕምሮው በቡልጋሪያ የሶፊያ ስቴት ኮንሰርቫቶሪ መደበኛ ትምህርቱን ገፍቶ የተካነው
“… ወደ ኢትዮጵያ 1995 .. ከተመለሰ በኋላ ግርማ ደረጃውን የጠበቀ ክላሲካል ትርዒት ምን እንደሚመስል ደርዝ ያለው ግንዛቤ ማስጨበጥን ሥራዬ ብሎ ከመያያዙ ሌላ፤ አዳዲስ የሙዚቃ ስራዎችን ፅፏል፡፡ ለነዚህ አዳዲስ የጥበብ ስራዎች መቀመሪያ ይሆነው ዘንድ የአውሮፓን የጥበብ መላ ከኢትዮጵያ ሙዚቃና ሥነ-ትውፊታዊ ዕሴት ጋር በማጋባት ተጠቅሟል፡፡....››


ከፍተኛ ሽያጭ ያስመዘገበው አዲሱ አልበሙ በአሜሪካ በቢልቦርድ ሰንጠረዥ 23 ደረጃ አግኝቷል ታዋቂው ፒያኒስት ግርማ ይፍራሸዋ በቅርቡ በአሜሪካ ያስመረቀው “Love and peace” የተሰኘ አዲስ አልበሙ፤ በቢልቦርድ ሰንጠረዥ 23 ደረጃ ላይ እንደተቀመጠለት ይናገራል፡፡ በአሜሪካ ያቀረበው ኮንሰርት እንደተወደደለት የገለፀው ፒያኒስቱ፤ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በአድናቆት የተሞላ ጽሑፍ እንዳወጣለት ጠቁሟል፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ኤልሳቤት ዕቁባይ ከግርማ ይፍራሸዋ ጋር ያደረገችው ቃለምልልስ እንዲህ ቀርቧል፡፡ ወደ ሙዚቃ እንዴት እንደገባ በመናገር ይጀምራል፡-


ሙዚቃ የጀመርኩት በልጅነቴ ክራር በመጫወት ነው፡፡ ክራር ስጫወት ነው ያደግሁት፡፡ ፡፡ሙዚቃን በሳይንሳዊ መንገድ ለማጥናት ደግሞ  ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት በመግባት፤ ከባህል ክራር፣ ከዘመናዊ ደግሞ ፒያኖን ለአራት አመት ተማርኩ፡፡ የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ትምህርቴን እንዳጠናቀቅሁ፣  1980 ስኮላርሺፕ አግኝቼ ወደ ቡልጋሪያ  አቀናሁ፡፡
እዚያ ከሄድክ በኋላ ግን ችግር ገጠመህ

Monday, August 18, 2014

የጳውሎስ መልእክት ወደ ኢትዮጵያ ሰዎች !

ርዕስ- ጳውሎስ ኞኞ (1926-1984)፣
የገፅ ብዛት - ከፎቶና ማጣቀሻ ጽሑፎች ዝርዝር ጋር 308፣
የሽፋን ዋጋ - 84 ብር (24 ዶላር)፣
የህትመት ዘመን - 2006 ዓ.ም
ህትመት - አርቲስቲክ ማተሚያ ድርጅት
ጸሐፊ - ደረጀ ትዕዛዙ

በዘመናችን ግለታሪኮችና ታሪኮች በብዛት ባይሆንም በተሻለ መጠን ለህትመት እየበቁ ናቸው፣ ይህ መልካም ጅምር መጠናከር ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም ዓለማችንን የቀየሩዋት ባለ ልዩ አዕምሮ ግለሰቦች ናቸው፤ በእነሱ ጥረትና የድካም ፍሬ ድምሩ ህዝብ ተጠቃሚ ሆኗል፤ ይሆናልም፡፡ እንኳንስ ተፈጥሮ አድልታ ባለ ምጡቅ አዕምሮ ያደረገቻቸው ግለሰቦች ይቅሩና የኔቢጤው በረንዳ አዳሪ ሁሉ ቀርቦ የሚያነበው ቢያገኝ ታላቅ መጽሐፍ ነው፤ ታላቅ መረጃ በውስጡ ይኖራል፡፡
ከነገስታትና ልኡላን ዜና መዋዕሎች በቀር እብዛም ያልተለመደ የነበረው የግለሰቦች ታሪክ በቤተሰቦቻቸው፣ ወይም መልካም ፈቃዱና ችሎታው ባላቸው ግለሰቦች አማካይነት እየተጻፈ ልምዳቸውን እንድንካፈል የላቀ ድርሻ እየተወጡ ናቸው፡፡ በቅርቡ ታትሞ ገበያ ላይ የዋለውና በጳውሎስ ኞኞ የህይወትና ሥራ ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነው መጽሐፍም ከእነዚህ የግለሰብ ታሪኮች የሚመደብ ነው፡፡
በዘጠኝ ምዕራፎች የተከፋፈለው የ“ጳውሎስ ኞኞ” መጽሐፍ፤ የተለያዩ ፎቶግራፎችንና ውሱን ሰነዶችንም አካትቷል፡፡ ስለጳውሎስ ልደት፣ ዕድገት፣ ትምህርት፣ ሥራና ባህርይ የሚያትተው ይህ መፅሀፍ፤ ከጳውሎስ ጋር ባላንጣ ስለነበሩት የወቅቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር ደጃዝማች ግርማቸው ተክለሐዋርያትም የሚያካፍለን ቁም ነገር አለ፡፡
ጳውሎስ ያልሞከረው ሥራ የለም ማለት ይቻላል፤ ግለሰብ ሱቅ ውስጥ ተቀጥሮ መስራት የጀመረው ገና በልጅነት ዕድሜው ሲሆን ትምህርቱን ከአራተኛ ክፍል ያቋረጠውም በድህነት ምክንያት ነው፡፡ (ገፅ 16) ከግሪካዊው ኞኞ እና ከኢትዮጵያዊቷ ወ/ሮ ትበልጫለሽ ቁልቢ ገብርኤል አካባቢ የተወለደው ጳውሎስ፤ የልጅነት ህይወቱ የተመሰቃቀለ ነበር፡፡ እናቱ ፍጹም ድሃ በመሆናቸው እንደ እመጫት ድመት በየቦታው ይዘውት ስለሚዞሩ በትምህርቱ ላይ ጫና መፈጠሩ የግድ ነበር፡፡

Wednesday, June 18, 2014

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ኢስተር ራዳ ከአመቱ 50 የዓለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ አይሁዳውያን አንዷ ሆነች

አዲስ አድማስ

የእስራኤል ፕሬዚዳንት፣ ጠ/ሚንስትር፣ የገንዘብ ሚ/ር እና የኢኮኖሚ ሚ/ር በዝርዝሩ ውስጥ ተካተዋል
ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ታዋቂ ድምጻዊት ኢስተር ራዳ፣ ‘ዘ ጀሩሳሌም ፖስት’ ጋዜጣ የአመቱ የዓለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ አይሁዳውያን ብሎ ከመረጣቸው 50 ታዋቂ ግለሰቦች መካከል አንዷ ሆነች፡፡


  በሶል፣በአር ኤንድ ቢ እና በፋንክ ስልቶች የተቃኙና የኢትዮ-ጃዝ ቃና ያላቸው ሙዚቃዎችን የምትጫወተውና “የእስራኤል የሶል ሙዚቃ ንግስት” በመባል የምትጠራዋ ኢስተር ራዳ፣ በእስራኤል ብቻም ሳይሆን በመላ አለም በርካታ አድናቂዎችን ማፍራት የቻለች ድምጻዊት መሆኗን ‘ዘ ጀሩሳሌም ፖስት’ ባለፈው ሰኞ ይፋ ባደረገው መረጃ መስክሮላታል፡፡
ጋዜጣው ተስፋ ከሚጣልባቸውና ከፍተኛ ስኬት ካስመዘገቡ የዘመኑ ተጠቃሽ ቤተ እስራኤላውያን አርቲስቶች ተርታ ትሰለፋለች ያላት ይህቺ ድምጻዊት፣ በተለያዩ ጊዜያት በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ስኬታማ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን ማቅረቧንና፣ ኢትዮጵያዊ ቅኝት ያላቸውን ሙዚቃዎች እንደምትጫወትም ገልጧል፡፡
በሙዚቃው ዘርፍ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ማፍራትና ለኤምቲቪ አውሮፓ የሙዚቃ ሽልማት እስከመታጨት የደረሰችው ኢስተር ራዳ፣ ‘ኪሮት’ እና ‘ስቲል ዎኪንግ’ን በመሳሰሉ ፊልሞች፣ ሙዚቃዊ ቲያትሮችና ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ በተዋናይነት በመስራት ድንቅ የትወና ክህሎቷን አስመስክራለች፡፡
በተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚኖሩ ፖለቲከኞች፣ ተመራማሪዎች፣ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች፣ ስራ ፈጣሪዎች፣ ቢሊየነሮች፣ አርቲስቶችና በሌሎች ሙያዎች ላይ ተሰማርተው ውጤታማ መሆን የቻሉ ግለሰቦችን በዘንድሮው የአመቱ 50 የአለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ አይሁዳውያን ዝርዝር ውስጥ ያካተተው ዘ ጀሩሳሌም ፖስት፤ ከእነዚህም ውስጥ ኢስተር ራዳን ጨምሮ 15 ያህሉ ሴቶች መሆናቸውን ይፋ አድርጓል፡፡
ካቻምና በእስራኤል ጠ/ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ፣ አምና ደግሞ በገንዘብ ሚንስትሩ የር ላፒድ ተይዞ የነበረውን የዚህ  ዝርዝር መሪነት፣ ዘንድሮ የአሜሪካ ትሬዠሪ ጸሃፊ የሆኑት ጃክ ሊው ተረክበውታል፡፡ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ቁልፍ ሚናን በሚጫወተው በዚህ ዘርፍ ውስጥ ጉልህ ሚና እየተጫወቱ የሚገኙት እኒህ ሰው፣ በፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አስተዳደር ውስጥ ተጽዕኖ መፍጠር የቻሉ ተሰሚ ሰው እንደሆኑ ጋዜጣው ዘግቧል፡፡
በተጽዕኖ ፈጣሪነት ሁለተኛውን ደረጃ የያዙት አሜሪካዊቷ ቤተ እስራኤላዊ ጃኔት የለን ሲሆኑ፣ የአሜሪካን ተቀማጭ ገንዘብ ተቋም እንዲመሩ በመመረጥ በአገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ናቸው፡፡ እሳቸውን ተከትለው በዝርዝሩ የተካተቱት፣ ቤኒያሚን ኔታኒያሁ (የእስራኤል ጠ/ሚንስትር) እና ሽሞን ፔሬዝ (የእስራኤል ፕሬዚዳንት) ናቸው፡፡
አቪግዶር ሊበርማን (የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር)፣ የር ላፒድ (የእስራኤል የገንዘብ ሚንስትር) እና ናፋታሊ ቤኔትም (የእስራኤል የኢኮኖሚ ሚንስትር)፣ በዘንድሮው ተጽዕኖ ፈጣሪ ቤተ እስራኤላውያን ዝርዝር ውስጥ ከተካተቱ ታዋቂና በአለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ መፍጠር የቻሉ ግለሰቦች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

 http://www.addisadmassnews.com

Wednesday, April 2, 2014

ያ 'ትውልድ ይደገም



ጥጥ ነድፎ በደጋን አሸከርክሮ ፈትሎ
ማግ ሰርቶ ልቃቂት በእንዝርት ጠቅልሎ
ድሩን ወደ ሸማ በመቃ አስማምቶ
ከወትት የነጣ ጋቢ ኩታ ሰርቶ
ጥበብ ያለበሰኝ በወግ በመዕረግ
ይደገም ያ ትውልድ ይተካ ይመንደግ።

ኤዱዋርዶ

Monday, March 31, 2014

የኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ልጅ በእንግሊዝ መነጋገሪያ ሆኗል

  አንተነህ ይግዛው
ዴቪድ ካሜሮንን ጨምሮ 19 የእንግሊዝ ጠ/ ሚኒስትሮች የተማሩበት ታዋቂ ኮሌጅ ይገባል “ፖለቲከኛ ለመሆን የግድ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን የለብኝም!…” - ልጁ
“ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን አንጸባራቂ ኮከብ እንደሚሆን አምናለሁ!” - መምህሩ
በአገረ እንግሊዝ ያጡ የነጡ ድሆች ከሚኖሩባቸው አካባቢዎች አንዷ ናት - ኒውሃም፡፡
እዚህ ግባ የሚባል ገቢ የሌላቸውና ከመንግስት በሚያገኙት ድጎማ ከእጅ ወደአፍ ኑሮን የሚገፉ ድሃ ዜጎችና ስደተኞች የከተሙባት የምስራቅ ለንደኗ ኒውሃም፣ ከሰሞኑ የበርካታ ታዋቂ መገናኛ ብዙሃን የዜና ርዕስ ሆናለች፡፡
የድሆች መንደር ኒውሃም፣ በአንድ ልጇ ስሟ ተደጋግሞ ተጠራ። ነገ ከነገ ወዲያ የኒውሃምና የድሃ ነዋሪዎቿ ብቻ ሳይሆን፣ የመላ እንግሊዝ ተስፋ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት የተሰጠው ይህ ልጅ፣ ይስሃቅ አይሪስ ይባላል፡፡ ይስሃቅ አሁን፣ የመንግስት ተረጂ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኛ ወላጆቹ የአቶ አባተ እና የወ/ሮ በቀለች ብቻ ሳይሆን የኒውሃም ብሎም የእንግሊዝ ልጅ ነው፡፡ ከሰሞኑ ስለይስሃቅ የተሰማው ወሬ፣ ለወላጆቹ ብቻ አይደለም የምስራችነቱ - ለመላ ኒውሃም ነዋሪዎች ጭምር እንጂ፡፡
“የኒውሃሙ ይስሃቅ፣ የኤተን ኮሌጅ ተማሪ ሊሆን ነው!” ሲሉ ዘገቡ፣ እነ ቢቢሲና ዘ ጋርዲያን፡፡
ከኒውሃም ድሆች መካከል የሚኖረው ይስሃቅ፣ የሞላላቸው የእንግሊዝ ባለጸጎችና ታላላቅ የአገሪቱ መሪዎች ተመርጠው ወደሚገቡበት ቅጽር ግቢ ይገባ ዘንድ ተጠራ፡፡ በመንግስት ድጎማ ከሚተዳደር እዚህ ግባ የማባይል ተራ ትምህርት ቤት ወጥቶ፣ በአገረ እንግሊዝ ዝናቸው ከናኘ ኮሌጆች አንዱ ወደሆነው ታዋቂው ኤተን ኮሌጅ ሊገባ ነው፡፡
“ታዲያ ኮሌጅ መግባት አዲስ ነገር ነው እንዴ!?... የልጁ ኮሌጅ መግባት ዜናነቱ ምን ላይ ነው!?” የሚል ጥያቄ የሚሰነዝር አንባቢ፣ እሱ ልጁንም ኤተንንም በቅጡ የማያውቅ ሊሆን ይችላልና አይፈረድበትም።
ልጁ ይስሃቅ ነው፡፡ ከኒውሃም ድሆች መካከል በመንግስት ድጎማ ኑሯቸውን የሚገፉ የስደተኛ ኢትዮጵያውያን ወላጆች የአብራክ ክፋይ። በመንግስት ድጎማ በሚተዳደር እዚህ ግባ የማባይል የማህበረሰብ ትምህርት ቤት የሚማር ያልተመቸው ብላቴና፡፡ ግማሽ ያህሉ ተማሪዎች፣ ከመንግስት የሚሰፈርላቸውን የእለት ቀለብ እየተመገቡ የሚማሩበት ትምህርት ቤት ውስጥ ቀለም ሲቆጥር የሚውል ያልደላው ተማሪ፡፡
ኮሌጁ ደግሞ ኤተን ነው፡፡ ኤተን ዝም ብሎ ኮሌጅ አይደለም። እንኳን በመንግስት ድጎማ ለሚተዳደሩ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን፣ ለሞላላቸው እንግሊዛውያን ወላጆችም ልጅን ከፍሎ ለማስተማር የሚያዳግት ውድ ኮሌጅ፡፡ የተመረጡ ተማሪዎች የሚገቡበት፣ የላቁ ተመራቂዎች የሚወጡበት ዝነኛ ግቢ ነው - ኤተን፡፡ እንግሊዝ የወቅቱን ጠቅላይ ሚኒስትሯን ዴቪድ ካሜሮንን ጨምሮ፣ 19 ጠቅላይ ሚኒስትሮቿን ያገኘችው ከዚህ የተከበረ የልሂቃን አጸድ ውስጥ ነው፡፡
የድሃው ልጅ ይስሃቅ፣ በመንግስት ድጎማ ከሚተዳደር እዚህ ግባ የማባይል ተራ ትምህርት ቤት ወጥቶ፣ በአገረ እንግሊዝ ዝናቸው ከናኘ ኮሌጆች አንዱ ወደሆነው ታዋቂው ኤተን ኮሌጅ የመግባት ዕድል ማግኘቱ ነው፣ ነገርዬውን የእነ ዘጋርዲያን ትልቅ ወሬ ያደረገው፡፡
አንድ ዕለት…