ድፃዊት ራሄል ዮሃንስ ከአዲስ ድማስ ጋዜጣ ጋር
እንዴት ወደ ቤተመንግስት ለመቅረብ ቻልሽ?
ያኔ ቤተመንግስት ቱሪስቶች ሲመጡ አጉራሽ ይፈለግ ነበር፡፡ ቤተ-መንግስት ሄደን እንጀራ እናጎርሳለን፡፡ የቤተመንግስት እንጀራ እንደዚህ ሶፍት ነጭ ነበረ(በእጅዋ የያዘችውን ሶፍት እያሳየችኝ) ፈረንጆቹ ናፕኪን እየመሰላቸው እንጀራውን እንደ ሶፍት ይጠቀሙበታል፡፡ ቤተመንግስት ውስጥ በጣም ስለተቸገሩ--- እስኪ ቆነጃጅትን ፈልጉ ተባለ። አንድ እኔን በጣም የሚያውቅ ሰው ነበረ…ነፍሱን ይማርና ኮማንደር እስክንድር ‹‹ዋይን ገርል ራሄልን ጥሩ›› አለ፡፡ ዋይን ገርል ነበርሽ እንዴ?
አዎ፡፡ ዋይን ስፔሻሊስት ነኝ፡፡
እንዴት--- የት ተማርሽው?
ታሪኬ ብዙ ነው አላልኩሽም፡፡
እስቲ አውጊኛ ----
ዛሬ እንግዲህ አብረን ማደራችን ነው፡፡ ግዴለም አጫውቺኝ ---- ስሚ----.ድሮ ሁለቱን ልጆቼን እንደወለድኩ ባሌን ፈታሁ ከዛ ‹‹ራስ ሆቴል ኮርስ መውሰድ አለብኝ›› ብዬ አሰብኩና ለሶስት ወር ያህል የገበታ ዝግጅት (tabel set up) የእንግዳ መስተንግዶ አሰጣጥ (how to serve the guest) ሰለጠንኩ፡፡ እንግሊዝኛውም ሌላ ነው--- እንደ አሜሪካን ነው የምናወራው፡፡ የእኛ ትምህርት ቤት እንደአሁኑ ቀላል መስሎሻል---ከሶስተኛ ክፍል በኋላ በእንግሊዝኛ ነው የምታወሪው፡፡ በተለይ በእንግሊዝኛ አስተማሪ በኩል----እኛ የተማርንበት ዘመን ሌላ ነበር፡፡ በጣም ቆንጆ ትምህርት ቤት ነው የተማርነው ግን አልሰራንበትም፡፡ እኔን ያልሽ እንደሆነ ግን በጣም የገባኝ አራዳ ስለነበርኩ በወቅቱ ሰርቼበታለሁ፡፡ እና የ‹‹ዋይን ገርል›› ኮርስ ስጨርስ ምርጫ ተሰጠኝና ጊዮንን መረጥኩ፡፡ ያኔ የነበሩት ሆቴሎች በጣም ትንሽ ናቸው፡፡ ዋቢ ሸበሌ ገና እየተጠናቀቀ ነበር.........
http://www.addisadmassnews.com
No comments:
Post a Comment