እንግዳ ፡- ሃሎ! ኤፍ.ኤም!
ኤፍ.ኤም ፡- ሄሎ! ስም ማን ልበል!?
እንግዳ ፡- የማን የኔ!?
ኤፍ.ኤም ፡- አዎ!
እንግዳ ፡- ገርማሜ
ኤፍ.ኤም ፡- ከየት ነው?
እንግዳ ፡- ያለሁበት ነው?
ኤፍ.ኤም ፡- አዎ!
እንግዳ ፡- ከሰፈረ ሰላም
ኤፍ.ኤም ፡- ያባት ስም ማን ልበል?
እንግዳ ፡- የማን የኔ!?
ኤፍ.ኤም ፡- አዎ!
እንግዳ ፡- በለጠ!
ኤፍ.ኤም ፡- ምን ፈልገህ ነው?
እንግዳ ፡- ማን እኔ?
ኤፍ.ኤም ፡- አዎ!
እንግዳ ፡- ሙዚቃ ነዋ!
ኤፍ.ኤም ፡- የማንን ካሴት ነው?
እንግዳ ፡- ካሴቱ ነው?
ኤፍ.ኤም ፡- አዎ!
እንግዳ ፡- ከናንተው ነዋ!
ኤፍ.ኤም ፡- አይ ማን የዘፈነውን ነው የምትፈልጉት ማለቴ ነው፡፡
እንግዳ ፡- ማን እኔን ነው?
ኤፍ.ኤም ፡- አዎ!
እንግዳ ፡- «ጭር ሲል አል ልወድም» የሚለው ይሁንልኝ
ኤፍ.ኤም ፡- ጭር ሲል አይወዱም!?
እንግዳ ፡- ማን እኔ?
ኤፍ.ኤም ፡- አዎ!
እንግዳ ፡- ምን?
ኤፍ.ኤም ፡- ጭር ሲል አይወዱም ወይ!?...ይፈራሉ?
እንግዳ ፡- ማን?
ኤፍ.ኤም ፡- እርስዎ!
እንግዳ ፡- እንዴት ወንድ አይደለሁ እንዴ፡ ለምን ቸእፈራለሁ!?
ኤፍ.ኤም ፡- ታዲያ ለምን መረጡ?
እንግዳ ፡- ማን?
ኤፍ.ኤም ፡- እርስዎ!
እንግዳ ፡- ምኑን!?
ኤፍ.ኤም ፡- ሙዚቃውን
እንግዳ ፡- ስለምወደው ነዋ!
ኤፍ.ኤም ፡- ለማን ነው የመረጡት?
እንግዳ ፡- ምኑን?
ኤፍ.ኤም ፡- ሙዚቃውን?
እንግዳ ፡- እ! ለባለቤቴ ለድንቡልቃ
ኤፍ.ኤም ፡- ለማን አሉ?
እንግዳ ፡- ነገርኩህ እኮ!ባዶቤት ጥላኝ ለጠፋችው ለባለቤቴ ለድንቡልቃ ብያለሁ፡፡
ኤፍ.ኤም ፡- እሺ! ተቀብለናል
እንግዳ ፡- ምኑን!?
ኤፍ.ኤም ፡- ምርጫዎን!
እንግዳ ፡- ሆሆ! ለናንተ ማን አለና? ለባለቤቴ ድንቡልቃ እኮ ነው ያሉኩት!
ስልኩ ተቋረጠ፡፡
No comments:
Post a Comment