አንድ
የፋኖስ መብራት በግብሩ የኮራ፤
እንዲህ
ሲል ተጣላ ከብርጭቆ ጋራ፡፡
‹‹እኔ
ነኝ መብራቱ ብርሃን የምሰጥ፤
ጨለማን
አጥፍቼ የምገላልጥ፡፡
አንተ
ግን ከፊቴ እንዲህ ተደንቅረህ፤
ዙሪያዬን
ከበኸኝ እንዲያው ተገትረህ፡፡
አልገባኝም
ከቶ የምትሰራው ስራ፤
ብርሃኔ
ሩቅ ደርሶ ደምቆ እንዳያበራ፤
አንተን
ፈጠረብኝ መንገድ የምትዘጋ፡፡
እንቅፋት
እየሆንክ ስራዬን አታጥፋ ፤
ገለል
በል ከፊቴ ብርሃኔ ይስፋፋ፡፡››
‹‹አገልግሎቴማ
ከሆነብኝ ጥፋት፤
እውነት
ላንተ ከሆንኩህ እንቅፋት፡፡
ልሂድልህ››
ብሎ ሲለቅለት ቦታ፤
ከጎን
የነፈሰ የንፋስ ሽውታ፣
መጣና
መብራቱን አጠፋው ባንዳፍታ፡፡
አጭር
እየሆነ ተመልካችነቱ፣
መለየት
አቅቶት ጥቅሙን ከጉዳቱ፣
እወቁኝ
እወቁኝ እያለ ሲነሳ
ሰውም
እንደዚሁ ያመጣል አበሳ፡፡
(ዶ/ር ከበደ ሚካኤል)