Monday, November 16, 2015

’’ዜጎቿን ለማስራብ እየተጋች ያለች ሀገር ኢትዮጵያ !’’


ሰለሞን ዮሃንስ
እኔ ርሀብን የማውቀው ለሰዓታት ነው:: ለዚያውም ምን ያህል ሰዓት እህል ሳልቀምስ መቆየት እችላለሁ ብዬ የሞከርኳት የቅብጠት ቆይታ ፡፡ያጥወለመለኝን ፤ማይትያቃተኝን ፤ያዘፈዘፈኝን ፍጹም ያዛለኝን የያኔው ርሃቤ ከዛሬው ርሃብ ውሎ ካደረበትና የሚላስና የሚቀመሰውን ካየ ቀናት የተቆጠሩበት ወገኔ ጋር ፈጽሞ ለንጽጽር የሚቀርብ አይደለም፡፡ እኔስ ያኔ ያገኘሁትን አግበስብሼ ነፍሴ መለስአለች ፡፡
ዛሬስ ወገኔማ ማሳው ደርቆ ፤ጎተራው ባዶ ሆኖ ተስፋ በሌለው ውል የመጨረሻ ቀኑን ይቆጥራል፡፡
ርሃብ ስንት ቀን ይፈጃል? ብዬ ልፈላሰፍ አይዳዳኝም፤ ወገኔ የሚላስ የሚቀመስ አጥቶ አጥንቱ እተቆጠረ አይኑ እየፈጠጠ ሰውነቱ ተስለምሞልሞ መጨረሻውን ይጠብቃል  …እንስሳቱማ መንገዱን ጠርገውለታል ፡፡
ለዚህ ደግና ኩሩ አፈርገፊ ህዝብ ይህ አይገባውም ነበር ፡፡
ይህ ደግ ህዝብ የሚቀጣው ለምን ይሆን ???
ዛሬም የዩቱ የሙዚቃ ባንድ   አባለቱንቱን ወዴት ናችሁ  ? ቦብ ጌልዶፍስ ምነው ዝም አልክ ? ማይክል ጃክሰን  ሆይ መቃብሩን ፈንቅልና ከሙያ አጋሮችህ ጋር ድረስልን እንበለው?
ምን አይነት ጉድ ነው የተጠናወተን ?
ማነው እንባውን እያዘራ ኢትዮጵያን ርሃብና ርዛት ከምድርሽ አይጥፋ ብሎ አምርሮ የረገማት?
ምን አይነት ክፉ ቀን ነው ተጣብቶ አለቅ ያለን ?
ይሄ ሀገሩን የሚመግበው ገበሬ የማይደክመው ፍጡር ዛሬ ተረታሁ ብሎ ይጣራል የሰሚ ያለህ እያለነው ፡፡ ጎታው ባዶ ሆኖ መሬቱ ደርቆ የሚውዳቸው እንስሳቱ ሞተውበት ድፍርስ እንባውን እያነባ ባዶ ማረሻ ይዞ ተስፋው ተሟጦ የሚመጣውን ይጠባበቃል፡፡
ያች ምስኪን እናት የልጆቿ የርሃብ እሪታ ጸንቶባት ሰቆቃ መስማት ተስኗት ከልጆቼ በፊት እኔን አስቀድመኝ ብላ ፈጣሪዋን ብትማጸንም  ልጆቿን በሞት መነጠቅ አልቀረላትም፡፡
እሷም የታጠፈ አንጀትዋን መቀነት አድርጋ እንባዋን ታዘራለች፡፡
እኛስ ?
እኛ ደግሞ እዚህ በስሜታዊነት ብቻ ማዶለማዶ ሆነን በቃላትና ቁጥርን መባስተባበል ተጠምደን
ዒላማ አልባ የደነበሸ ጥይት እንተኳኮሳለን ፤
ድርቅ ሆነ ርሃብ ፤
10 ሆነ 15 ሚሊየን ፤
ሰሜን ሆነ ደቡብ ፤
ክርክራችን ለዚህ በርሃብ አንጀቱ ለታጠፈ ኢትዮጵያዊ ምን ይጠቅመወቀል እንጀራ ውይስ ውሃ ይሆነዋል?
የሰው ልጅ ክቡር እየወደቀ ነው፡፡
ሰው የሚበላ ይፈልጋል በውሃ ጥም ጉሮሮው ደርቋል…ርሀብ እሞሸለቀው ነው ፡፡

ይህ ደግና ኩሩ ህዝብ 90 ሚሊየን ቤተሰቡን በጫንቃው የተሸከመው ታታሪ ገበሬ አቅቶተታል ፡፡

የደፈረሰ እንባውን የሚያብስለት፤ርሀቡን የሚያስታግስለት ወገን ይፈልጋል ፡፡
ምዕራብያኑን ’’የስንዴያለህ  ???’’ ብለን በራቸውን ብናንኳኳ በራሰቸው የቤት ስራና ቅድሚያ በሚሰጡት ነገር ተጠምደዋልና ፤ ወደውስጣችን እንመለስ ፡፡
ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ወገናችን ተርበቧል ፤
ይህ ደግ ህዝብ አቅቶታል፡፡
ይህ ደግ ህዝብ እኛኝ ይሻል፡፡
አዎእኛኝይሻል …..ጎራውን እንተውውና …ለዚህ ጨዋና ኩሩ ህዝብ አሁኑኑ እንድረስለት፡፡
አሁኑኑ !!!!!
’’ዜጎቿን ለማስራብ እየተጋች ያለች ሀገር ኢትዮጵያ !’’……. ከሚል ስላቅ ለመዳን ትልቅ የቤት ስራ ይጠበቅብናል፡፡
መቼም ኢትዮጵያ ልጆቿን ለማስራብ እነደማትተጋ ይታወቃል፡፡

ተው በለው !

ተው በለው !


Published on Jan 11, 2014
New Ethiopian Music 2014 Addis Mulat - Tewbelew