በዲያቆን ዳንኤል ክብረት
ዓርብ ለቅዳሜ ምሽት፣ጳጉሜን አምስት 2002 ዓ/ም ማታ በኢትየጵያ ቴሌቭዥን ይተላለፍ የነበረውን የአዲስ ዓመት ዋዜማ እያየሁነበር፡፡ ከአሜሪካ የገባሁት በዚያው ቀን ነበርና ዕንቅልፌ ሊስተካከልልኝ ስላልቻ በደንብ ነበር የተከታተልኩት፡፡ እኩለ ሌሊት ሊደርስ ሲል ግን አንድ አሳዛኝ ነገር ተከሰተ፡፡ የማከብራቸው አርቲስቶች ወደ መድረኩ ተሰባስበው ወጡና በዚያች ታሪካዊት ቀን ታሪካዊውን ስሕተት ሰሩት፡፡ እኩለ ሌሊት ስድስት ሰዓት ሊሆን ሽርፍራፊ ሰኮንዶች ሲቀሩ «አዲሱ ዓመት ሊገባ ስለሆነ እንቁጠር» አሉና ወደ ኋላ አሥር፣ ዘጠኝ፣ ስምንት፣እያሉ እስከ ዜሮ ቆጠሩ፡፡
.
ከዚያም ከምሽቱ ስድስት ሰዓት ላይ አዲሱ ዓመት ገባ ብለው አወጁ፡፡ «የሊቃውንቱ ስሕተት እድሜ ሲያገኝ ሕግ ይሆናል» ይላሉ፡፡ በጥንት ጊዜ አውስትራልያ የገባ አንድ አውሮፓዊ አይቷት የማያውቅ አዲስ ፍጡር ያይና የሀገሬውን ነዋሪ «ይህቺ እንስሳ ማን ትባላለች?» ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ ያም የሀገሩ ነዋሪ «ካንጋሮ» ብሎ መለሰለት፡፡ ያም ሰው «ካንጋሮ» የምትባል እንስሳ አገኘሁ ብሎ ለዓለም ተናገረ፡፡ በሀገሬው ቋንቋ ግን «ካንጋሮ» ማለት «አላውቅም» ማለት ነበር፡፡ አንድ ሞኝ የተከለውን አምሳ ሊቃውንት አይነቅሉትም እንዲሉ ይሄው ስሟ ሆኖ ቀረ፡፡