Wednesday, May 29, 2013

‘ከሽፍታ’ የተሰረቀች ግጥም




ገና!

ከእናቴ ሆድ ሳለሁ፤
ጠላት ሲዝትብኝ ሰምቻለሁ።
በዳዴ ዘመኔም፣
በ“ወፌ ቆመችም!”፤
አውዴ ክፉ ነበር ለወሬ አይመችም።
እንደ ሚዳቋ ነፍስ እንደ ነብር ጥፍር፤
ስጋትም−ጭካኔም − ነበር የዕውቀቴ ስር።

“ተጨቆነኩ!”
“ተበደልኩ!”
“ተረገጥኩ!”
“ተገፋሁ!”
“ተቀማሁ!”።
”መሬቱ ጠላቴ፤
ሰማዩ ብሶቴ።
ተስፋ−ትዝታዬን ሊያጠፋ ለቃቅሞ፤
ባፈሙዝ ያየኛል ገዳይ ደጄ ቆሞ።” ወዘተ....

በእነዚህ ‘ምግቦች’ አድጎ ሰውነቴ፤
እኮ እንደምን አይሆን ‘ጥርጣሬ’ ሀብቴ?
መገርሰስ፣መደምሰስ፣ማሳደድ − ውበቴ?

ስለዚህ አይድነቅህ!
ቀርበህ ወደድከኝም፣ርቀህ ጠላኸኝም፤
ገድዬህ ካላለፍኩ የኖርኩ አይመስለኝም።
 በረከት በላይነህ
 

No comments:

Post a Comment