ሀገራችን ኢትዮጵያ ገና ያልተጠኑ የበርካታ ጥንታዊ
ሥነጽሁፎች ባለቤት ናት፤ ማጥናት አቅቶን ሌሎች አጥንተው የቅጂ መብቱን ከመውሰዳቸውና የታሪክ ክፍትት ተፈጥሮ
በመጪው ትውልድ ተወቃሾች ከመሆናችን በፊት የዘርፉ ምሁራን ጥናትና ምርምር በማካሄድ፣ ዩኒቨርስቲዎች ጉዳዩን
የምርምር አቅጣጫቸው ውስጥ በማስገባት፣ ዜጎችም ጥንታዊ የጽሁፍ ሃብታችንን አስፈላጊነት ተገንዝበን ከዘራፊዎች
በመጠበቅ ሃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል፡፡ ኢትዮጵያ ዘመናትን ያስቆጠሩ ሥነቃላዊና የጽሁፍ ፍልስፍናዎች ባለቤት
ናት፡፡ ከአስራ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በፊት ከሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች በተለየ መልኩ በርከት ያሉ የፍልስፍና
ስራዎችን በመስራት በቀዳሚነት የምትጠቀሰው ኢትዮጵያ፤ በጥንታዊው የግእዝ ቋንቋ ከተጻፉት የፍልስፍና ስራዎቿ መካከል
ከፊሎቹን በትውልድ ካናዳዊ፣ በምርጫ ደግሞ ኢትዮጵያዊ የሆነው ፕሮፌሰር ክላውድ ሰምነር ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ
በመተርጎም፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቁ ሲያደርግ፤ ሌሎች በርካታ በግዕዝና በአረብኛ ቋንቋዎች የተጻፉ የጽሁፍ
ስራዎች በጥንታዊ ቤተእምነቶችና ቤተመዛግብት ውስጥ ተቀምጠው ክላውድ ሰምነርን የመሰሉ ፈላስፎችንና የጥንታዊ ጽሁፎች
ተመራማሪዎችን (philologists) እይታ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
Wednesday, May 15, 2013
Saturday, May 11, 2013
Ethiopia Detains Top Taxmen
![]() | |
| Melaku Fenta and Gebrewahid Woldegiorgis |
Melaku Fenta, director of the Ethiopian Revenues & Customs Authority (ERCA), who has retained his position since 2008 at the inception of ERCA is the most prominent name on the list. Gebrewahid Woldegiorgis, deputy director of ERCA is the second name listed by the state media.
The names of the other 14 detainees have not been released.
http://addisfortune.net/breaking-news/top-ethiopian-govt-officials-detaines/
Wednesday, May 8, 2013
ዳንኪራ.... Dan-Kira
The word means Dan-Kira dancing rhythmically by hitting the ground with your feet’’ in Ethiopia founded by Mr Daniel Dulla and Mr Daougi Teddy in 2007 as international entertainment company. Dan-Kira award winner on 2011 BEFFTA Awards (Black Entertainment Film Fashion Television and Arts) best dance act categories.
Dan-Kira entertainment providing the highest quality of east African traditional performance, set up east African live music and theatre event in UK and all over the world and also giving a short course for the people who is interested learning east African dance. Our classes suitable for all age categories that stretches an east African people to give a confidence in deliberately uniqueness on professionally, incorporate an east African people who native and live in UK.
Our folk dance is one of the symbols of unique culture in the world. Dan-kira entertainment features perform all east African dance styles of showbiz performing at various social gatherings anywhere in the world. We make available more than twenty-five different tribes of dances and beat by changing amazing traditional colourful and well-designed outfit.
The style of our dance most of them traditional but we manage to make them appropriate for different audience that makes us Dan-Kira more gracefully as a traditional performer highly professionally.
Our shoulder, chest, body pumping and neck dances that make us unique, as we get feedback from many of previous performances as well as BBC radio WOMAD festival 2010.
http://www.reverbnation.com/dankiraentertainmenteastafricandancegroup
Tuesday, May 7, 2013
ይድረሥ ለሰራዊት ፍቅሬ (ግራ የሆነውን ግራና ቀኝ በተመለከተ)
በመጀመሪያ፤ ይህ ፅሁፍ ቀድሞ የተዘጋጀ የነበረው፣ለአዲሰ አድማሰ ጋዜጣ ነበር፡፡ሳይወጣ በመቆየቱ ወደዚህ አምተነዋል፡፡እናም ወደኋላ መለስ ብላችሁ አንብቡልኝ፡፡ እሱ በማያይበት መፃፌ ብቻ ሀሜት እንዳይመስልብኝ ሰጋሁ፡፡ ቢሆንም ጀመርን……
.
.
ሰላም ላንተ ይሁን ሠራዊት ፍቅሬ! እንደምን አለህ! የሕይወት ‹‹ግራ እና ቀኝ እንዴት ይዞሃል?? ይህችን ፅሁፍ (ደብዳቤ) የምጽፍልህ ‹‹ርዕዩት›› በተባለው የሬድዮ ፕሮግራም ላይ እንግዳ ሆነህ በቀረብክ ጊዜ ‹‹ታነባለህ ወይ›› ተብለህ ለቀረበልህ ጥያቄ ‹ግዴታ ሆኖብህ› እንደምታነብ ስትገልጽ በመስማቴ መልዕክቴ ባክኖ አይቀርም በሚል የፀና እምነት ነው፡፡ ታዲያ ስታነባት ግልጽ የሆነችና በቅን ልቦና የተፃፈች መሆኗን ተገንዘብልኝ፡፡
የፅሁፌም ሙሉ ትኩረት ፣ ግራ እና ቀኝ የተሰኘው ፕሮግራምህ ነው፡፡ በየሳምንቱ በፕሮግራሙ ላይ የሚስተናገዱ ‹‹ሃሳብ አልባ›› ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው ሃሳብ እንድሰነዝር ያስገደደኝ፡፡ እንደውም እንደውም ሳስበው እስካሁን ድረስ ርዕሱ እንጂ ፕሮግራም አልጀመራችሁም ባይ ነኝ ፣ ርዕሱ እየመራችሁ እንጂ ፕሮግራሙን እየመራችሁ አይደለም፡፡ እስካሁን በተላለፉት ፕሮግራሞቻችሁ ያየሁትም ‹‹ግራ እና ቀኝ›› ሊቀመጡ የማይችሉ ሃሳቦችን ጭምር በግብታዊነት እያነሳችሁ አቆማችኋቸው እንጂ ፣ እንኳን በአንድ ትልቅ የአገሪቱ ሚዲያ ቀርቶ ለእርስ በእርስ የወዳጅ ጨዋታ እንኳ የሚበቁ አይደሉም፡፡……. ሠራዊት ፣ የፕሮግራሙ ታላቁ ችግር ምን መሰለህ …. ያገኛችሁትን ማምጣታችሁ ፣ ያመጣችሁትን መወርወራችሁ፡፡ ይህንን የምለው ከምንም ተነስቼ አይደለም ፣ ከራስህ አባባል ተነስቼ ነው፡፡ በሊያ መጽሄት ቅፅ2 ቁጥር 17 የታህሳስ እትም ላይ በሰጠኸው ቃለ ምልልስ አንድ ቦታ እንዲህ አልክ ፤ ‹‹…. ሃሳብህ ምንም ይሁን ምን ወርውረው››…አየህ ሠራዊት ‹‹ምንም ይሁን ምን›› እያላችሁ የምትወረውሩዋቸው ፣ ምንም ያልሆኑ ርዕሶች ናቸው የፕሮግራሙ ስብራቶች፡፡
Thursday, May 2, 2013
‹‹ያምራል ብለው ከተናገሩት…››ከኑሮ እና ፖለቲካ /ቁጥር - 2 የተወሰደ/ በኃይሉ ገ/እግዚአብሔር
ሰውየው አርቲስት ነው፡፡ ወዳጄ
እንዳጫወተኝ፡፡ ማታ ማታ ሰክሮ ወደ ቤቱ ይገባል አሉ፡፡ ትህትና ይዞን ‹‹ማታ›› እንበልለት እንጂ እርሱስ የሚገባው ለጠዋት
በቀረበ ሰዓት ነው አሉ፡፡ ይህ አርቲስት እቤቱ እንደገባ የመጀመሪያው ተግባሩ ልጆቹን መቁጠር ነው፡፡
አሳዛኙ ነገር ልጆቹ ለመቆጠር
ብለው ከሚያምር እንቅልፍ ላይ ሁሌ እንዲነሱ መገደዳቸው ነው፡፡ ሲዘገንን! ለመሆኑ ልጆቹ ስንት ናቸው? አራት፡፡ ‹‹አንድ፣
ሁለት፣ ሦስት፣… ቆይ ! ቆይ ! ቆይ ! ተሳሳትኩ እንዴ ! እናንተ ሁላችሁም ቀጥ
ብላችሁ ቁሙ፤ አንድ፣ ሁለት፣ እ… አንተ ትንሹ ና ከፊት ሁን፤ አዎ ! አንድ፣ ሁለት፣ ሦ.. አይ!
አይ! ከሴት መጀመር አለበት፤ ነይ አንቺ ከፊት፤ አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት..›› እያለ ሲቆጥር ይነጋል አሉ ሌሊቱ፡፡ /የዚህ
ሰውዬ ቤተሰብ አባል ከመሆን ያዳነን እግዚሃር ምስጋና ይግባው አቦ !/
‹‹ሚስቴን እወዳታለሁ፤
ባለቤቴን እወደዋለሁ፤ በፍቅር የማምን ሰው ነኝ፤ ባለቤቴ ሕይወቴ፤ ሚስቴ ማለት እናቴ፤ ፍቅር ሰጥቶ ፍቅር የሚቀበል ጓደኛ
አለኝ፡፡ ልጆቼ፣ ጌጦቼ…›› ዓይነት የታዋቂ ሰዎችን ዲስኩር በመጽሔትና በጋዜጣ ማንበብ፤ እንዲሁም በቴሌቪዥን እና በሬዲዮ
ማየት እና ማድመጥ የለመድነው ጉዳይ ነው፡፡
እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ
አባት ሁሉ፣ ‹‹ሚስቱ ማለት አገልጋዩ፣ እጮኛው ማለት የስጋ ፈቃድን ከማሟያ ውጪ ትርጉም የሌላት፣ ልጆቹ ማለት በሞቅታ
ከደካከመ በኋላ ማታ መጥቶ ኮርኩሞ የሚያስተኛቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ገመና ነውና በሚዲያው በኩል ወደ አደባባይ ሲወጣ
የቅድስናን ካባ ለራሱና ለጎጆው ያለከልካይ ይሸልማል፡፡ /‹‹ለምን ይዋሻል?›› አለ ኮሜዲያን ተስፋዬ ካሣ!/
Subscribe to:
Posts (Atom)
-
ተስፋሁን 21 ዓመቱ ነው፡፡ከ ፍቅረኛ ጋር አንድ ሰፈር ናቸው የሚማሩትም አንድ ትምህርት ቤት ነው ይህ ደግሞ የበለጠ እነዲግባቡ አስቸሎዋቸዋል፡፡አብረው ይሄዳሉ አብረው ይመለሳሉ…ካፌ ዘና ይላሉ በቃ አሪፍ ...
-
አንድ የፋኖስ መብራት በግብሩ የኮራ፤ እንዲህ ሲል ተጣላ ከብርጭቆ ጋራ፡፡ ‹‹ እኔ ነኝ መብራቱ ብርሃን የምሰጥ፤ ጨለማን አጥፍቼ የምገላልጥ፡፡ አንተ ግን ከፊቴ እንዲህ ተደን...
-
ላለፉት 15 አመታት በፊልም ሙያ ላይ የተሰማራው ቴዎድሮስ ተሾመ፤ በፊልም ፅሁፍ ደራሲነት፣ በተዋናይነት፣ በዳሬክተርነትና በፕሮዲዩሰርነትም ሰርቷል፡፡ በሙያ ዘመኑ አምስት ፊልሞችን ሰርቶ ለእይታ ያበቃው አርቲስቱ፤ ...




