ዛሬ በማህበራዊ ድረገጽ ከተቀባበልናቸው ነገሮች ታሪካዊ ቀንነቱን በመንተረራስ ዳግማዊ አጤ ምኒልክና
(እምዩ ምኒልክ)
እቴጌ ጣይቱ (ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ) የተወለዱብት ቀን ዝክርን ነው ፡፡
እኔም ካየሁት ላካፍላችሁ
- ሰው ሁሉ እኩል ስለሆነ ማንም
ሰው ሰውን ባሪያ አይበል ።
- ሁሉም ሰው በየኃይማኖቱ ይደር ።
- ድኻ እወደደበት ቦታ ይቀመጥ ። በዘር ፣ በወገን ልዩነት አይከልከል ።
- የመሬት ጥያቄ ላቀረቡ የውጭ አገር ሰዎች ንጉሡ የሰጡት መልስ፡- ‹‹ የኛ አገር ፍትሐ ነገሥት ልዑሎች መሬት ይሽጡ አይልም ። ያገሬ መሬት ባለቤቱ ሌላ ነው ። ከአባቶቻቸው እየተቀበሉ ያቆዩት መሬት ነው ።... መሬቱ የሁሉም ስለሆነ አይሸጥም ። ማንም ሰው መሬቱን ሊሸጥ አይችልም ። መሬትን መሸጥ፣ መስጠትም የሚችለው የመሬቱ ጌታ ነው ››
- ለመንግሥት ተሿሚዎች የሰጡት መመሪያ፡- ‹‹… እንቅልፍ ሳትወዱ ፣ መጠጥ ሳታበዙ፣ ገንዘብን ጠልታችሁ ተግታችሁ ሥራችሁን ፈጽሙ ። እኔ እናንተን ስለአመንኩ እናንተም የምታምኑትን ፣ ገንዘብ የማይወደውን፣ ድኻ የማይበድለውንና የሚረዳችሁን ሰው እያመለከታችሁኝ ከሥራው በመግባት መንግሥታችንን እርዱ ››
- በጣም ወደኋላ የቀረን ሕዝቦች ነን ። ገና የሚሠራ ብዙ ሥራ ስላለ ወጣቶቻችን መማር አለባቸው ።
- አባት ያለህ የአባትህን እሰጥሀለሁ፤ አባትህን መርቅ ። አባት የሌለህ አባትህ እኔ ነኝና ደጅ ጥናኝ ።
- እኔ ቤት እንጀራ የለም ። እንጀራ ያለው ትምህርት ቤት ስለሆነ ፤ እሠራሁት ትምህርት ቤት ልጆቻችሁም እያስገባችሁ አስተምሩ ።
- የኔ ርስት ኢትዮጵያ ናት ፤ የግል ርስት አልፈልግም ። ደግሞስ የተሾምነው እርስት ከተካፈልን ለሕዝቡ ማን ያካፍለዋል?
- ሐገራችን አንድትለማ የሚቀርቡንን ሁሉ በታላቅ ደስታና በአክብሮት እንቀበላቸዋለን ። በሌላ ለሚመጡብን ግን ፤ ሁላችን ሳናልቅ ሀገራችንን ለባዕድ አሳልፈን እንሰጥም ።
- የሚጠሉህን ሰዎች ከማጥፋት ፤ የሚጠላብህን ማጥፋት እንዲሉ ፤ የሸፈቱባቸውን ፣ የወጉአቸውንና ያሤሩባቸውን ሰዎች በጋብቻ ፣ በዝምድና ወይም ወዳጅ አድርገው ያቀርባሉ እንጂ ክፉን በክፉ መመለስና መበቀልን አይሹም ።
- አንድ የፈረንሳይ ዜጋ የቦታ ግዥ ፈቃድ ሲጠይቃቸው ምኒልክ በሰጡት መልስ ፡- ‹‹ ያገሬ መሬት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ስለሆነ ፤ መሬት መሸጥ መለወጥ የሚችለው ሕዝቡ ነው ። ደግሞስ የውጭ ዜጎች መሬት እንዲገዙ ከፈቀድኩና ባለመሬት ከሆኑ ፤ ለኔ ምን ቀርቶ እገዛለሁ ? ›› አሉ ።
እቴጌ ጣይቱ ብጡል ለወራሪውና ለፋሺስቱ ጣልያን ከተናገሩት ታሪካዊ ንግግር በከፊል
: -
" እኔ ሴት ነኝ ፡፡ ጦርነት አልወድም ፤ ነገር ግን ሀገሬን እንደዚህ ያለ
ክብር የሚነካ ዘለፋ ከምትሸከም ጦርነትን እመርጣለሁ ፡፡ ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ ! እግሩን ለጠጠር ደረቱን ለጦር አስጥቶ
ደሙን ለሀገሩ ፍቅር አፍስሶ ለአፈሩ ክብር ለብሶ እሱ ወድቆ ሀገሩን የማያቆም እዚህ ያለ እንዳይመስልህ ! ሂድ! የኢትዮጲያን ሰው
ባታውቀው ነው፡፡ ለሀገሩ መሞት ማለት ለሀበሻ ጌጡ ነው ፡፡ ሂድ ባሻህ ግዜ ተመለስ ተሰናድተን እንጠብቅሃለን ፡፡ ያንተን ወንድነትና
የጣይቱን ሴትነትም ያን ግዜ እናየዋለን ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ ፡፡ "
ስለሰውነት ክብር ፣ ስለሀገር ነፃነት ለሚቆረቆሩት ለእምዬ ምኒልክ 171 ኛ እና ለእቴጌ
ጣይቱ ብጡል 175 ኛ መልካም የልደታቸው መታሰቢያ ዕለት ይሁን !!!
" ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር "