Tuesday, August 18, 2015

ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ከተናገሯቸው ታሪካዊ ንግግሮች በጥቂቱ !

ዛሬ በማህበራዊ ድረገጽ  ከተቀባበልናቸው ነገሮች ታሪካዊ ቀንነቱን በመንተረራስ ዳግማዊ አጤ ምኒልክና (እምዩ ምኒልክ)
እቴጌ ጣይቱ (ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ) የተወለዱብት ቀን ዝክርን  ነው ፡፡

እኔም ካየሁት ላካፍላችሁ



- ሰው ሁሉ እኩል ስለሆነ ማንም ሰው ሰውን ባሪያ አይበል ።
- ሁሉም ሰው በየኃይማኖቱ ይደር ።

-
ድኻ እወደደበት ቦታ ይቀመጥ ። በዘር ፣ በወገን ልዩነት አይከልከል ።

-
የመሬት ጥያቄ ላቀረቡ የውጭ አገር ሰዎች ንጉሡ የሰጡት መልስ፡- ‹‹ የኛ አገር ፍትሐ ነገሥት ልዑሎች መሬት ይሽጡ አይልም ። ያገሬ መሬት ባለቤቱ ሌላ ነው ። ከአባቶቻቸው እየተቀበሉ ያቆዩት መሬት ነው ።... መሬቱ የሁሉም ስለሆነ አይሸጥም ። ማንም ሰው መሬቱን ሊሸጥ አይችልም ። መሬትን መሸጥ፣ መስጠትም የሚችለው የመሬቱ ጌታ ነው ››

-
ለመንግሥት ተሿሚዎች የሰጡት መመሪያ፡- ‹‹… እንቅልፍ ሳትወዱ ፣ መጠጥ ሳታበዙ፣ ገንዘብን ጠልታችሁ ተግታችሁ ሥራችሁን ፈጽሙ ። እኔ እናንተን ስለአመንኩ እናንተም የምታምኑትን ፣ ገንዘብ የማይወደውን፣ ድኻ የማይበድለውንና የሚረዳችሁን ሰው እያመለከታችሁኝ ከሥራው በመግባት መንግሥታችንን እርዱ ››

-
በጣም ወደኋላ የቀረን ሕዝቦች ነን ። ገና የሚሠራ ብዙ ሥራ ስላለ ወጣቶቻችን መማር አለባቸው ።

-
አባት ያለህ የአባትህን እሰጥሀለሁ፤ አባትህን መርቅ ። አባት የሌለህ አባትህ እኔ ነኝና ደጅ ጥናኝ ።

-
እኔ ቤት እንጀራ የለም ። እንጀራ ያለው ትምህርት ቤት ስለሆነ ፤ እሠራሁት ትምህርት ቤት ልጆቻችሁም እያስገባችሁ አስተምሩ ።

-
የኔ ርስት ኢትዮጵያ ናት ፤ የግል ርስት አልፈልግም ። ደግሞስ የተሾምነው እርስት ከተካፈልን ለሕዝቡ ማን ያካፍለዋል?

-
ሐገራችን አንድትለማ የሚቀርቡንን ሁሉ በታላቅ ደስታና በአክብሮት እንቀበላቸዋለን ። በሌላ ለሚመጡብን ግን ፤ ሁላችን ሳናልቅ ሀገራችንን ለባዕድ አሳልፈን እንሰጥም ።

-
የሚጠሉህን ሰዎች ከማጥፋት ፤ የሚጠላብህን ማጥፋት እንዲሉ ፤ የሸፈቱባቸውን ፣ የወጉአቸውንና ያሤሩባቸውን ሰዎች በጋብቻ ፣ በዝምድና ወይም ወዳጅ አድርገው ያቀርባሉ እንጂ ክፉን በክፉ መመለስና መበቀልን አይሹም ።
- አንድ የፈረንሳይ ዜጋ የቦታ ግዥ ፈቃድ ሲጠይቃቸው ምኒልክ በሰጡት መልስ ፡- ‹‹ ያገሬ መሬት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ስለሆነ ፤ መሬት መሸጥ መለወጥ የሚችለው ሕዝቡ ነው ። ደግሞስ የውጭ ዜጎች መሬት እንዲገዙ ከፈቀድኩና ባለመሬት ከሆኑ ፤ ለኔ ምን ቀርቶ እገዛለሁ ? ›› አሉ ።
እቴጌ ጣይቱ ብጡል ለወራሪውና ለፋሺስቱ ጣልያን ከተናገሩት ታሪካዊ ንግግር በከፊል : -
" እኔ ሴት ነኝ ፡፡ ጦርነት አልወድም ፤ ነገር ግን ሀገሬን እንደዚህ ያለ ክብር የሚነካ ዘለፋ ከምትሸከም ጦርነትን እመርጣለሁ ፡፡ ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ ! እግሩን ለጠጠር ደረቱን ለጦር አስጥቶ ደሙን ለሀገሩ ፍቅር አፍስሶ ለአፈሩ ክብር ለብሶ እሱ ወድቆ ሀገሩን የማያቆም እዚህ ያለ እንዳይመስልህ ! ሂድ! የኢትዮጲያን ሰው ባታውቀው ነው፡፡ ለሀገሩ መሞት ማለት ለሀበሻ ጌጡ ነው ፡፡ ሂድ ባሻህ ግዜ ተመለስ ተሰናድተን እንጠብቅሃለን ፡፡ ያንተን ወንድነትና የጣይቱን ሴትነትም ያን ግዜ እናየዋለን ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ ፡፡ "
ስለሰውነት ክብር ፣ ስለሀገር ነፃነት ለሚቆረቆሩት ለእምዬ ምኒልክ 171 ኛ እና ለእቴጌ ጣይቱ ብጡል 175 ኛ መልካም የልደታቸው መታሰቢያ ዕለት ይሁን !!!
" ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር "

1 comment:

  1. Best 7 Casino Sites in Michigan 2021 - Dr.MD
    Best 7 Casino Sites in Michigan 부천 출장마사지 2021 · 1. SugarHouse NJ, USA · 2. 888 Casino, USA · 3. BetMGM Casino, 익산 출장안마 USA · 4. 춘천 출장안마 888 충주 출장샵 Casino, USA · 5. BetMGM Casino, USA · 6. Wild Casino, USA 용인 출장마사지 · 7.

    ReplyDelete