Saturday, July 6, 2013

50 ወርቃማ ዓመታትን ከአሊ ቢራ ጋር!

ክቡር ዶ/ር አሊ ቢራ (በመዝገብ ስሙ አሊ መሐመድ) የ5 ዓመት ወጣት ሳለ የተቀላቀለውን ‘አፍራን ቃሎ‘ የተሰኘ ለሱ የመጀመሪያው ባሕላዊ የኪነት ቡድን ውስጥ በመግባት የሙዚቃውን ዓለም በይፋ የተቀላቀለበትን 50ኛ ዓመት ከመላ ኢትዮጵያውያን‘ጋ እያከበረ ነው። የሙዚቃ ባንዱ ሦስት አሊዎች ስለነበሩት ለመለያነት በወቅቱ በአሊ ተጽፎ፣ ከፍተኛ ተወዳጅነት አግኝቶ በነበረው ዜማው "Birra Dha Nhaabarhie (ቢራ‘ዻ ናበሬ: የብራ መውጣት)" ከሚለው ዘፈኑ ተወስዶ አሊ ቢራ ተባለ።

አሊ ቢራ ለ50 ዓመታት ያክል በተለይ ለኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን የኑሮ ማጀቢያ ሙዚቃ ሆኗቸው ኖሯል። ከጊዜ ወደጊዜ ወደ የርዕዮተ ዓለማዊ ጥያቄ እየያዙ የመጡት ዘፈኖቹ ለኦሮሞ ሕዝብ ትግል ትልቅ ፋይዳም አላቸው። አሊ ከኦሮምኛ በተጨማሪ በአማርኛ፣ ሶማልኛ፣ አደርኛ፣ አረብኛና እንግሊዝኛ ዘፈኖችን ተጫውቷል።

አሊ በ1963 የመጀመሪያውን የኦሮምኛ አልበም አሳትሟል።

አሊ ቢራ በሙዚቃው ዓለም ላበረከተው አስተዋፅዖ በርካታ ሽልማቶችን ያገኘ ሲሆን ከጅማ ዩንቨርስቲም በ2003 የክብር ዶክትሬት ተበርክቶለታል። 



No comments:

Post a Comment