የሁለቱ አገራት ጨዋታ ጷጉሜ  ወር ላይ በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ዋና ከተማ  ባንጉይ መካሄድ የነበረበት ቢሆንም ፥  በአገሪቱ ያለው 
የፀጥታ ሁኔታ ጨዋታውን ለማካሄድ የሚያስችል ባለመሆኑ ተለዋጭ አስተናጋጅ አገር ሲፈላለግ ቆይቷል ። 
በፈረንጆቹ መስከረም 7  በብራዛቪል 
የሚካሄደውን የኢትዮጵያና  የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ
ጨዋታንም የሚዳኙ አራት ዳኞች ከአልጄሪያ  መመረጣቸውንም  ፊፋ  ጨምሮ
ገልጿል ።
ስለጨዋታው ያነጋገርናቸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን
ዋና  አሰልጣኝ አቶ ሰውነት ቢሻው ውደድሩ  የሚካሄድበት ቦታ ሞቃታማ ቢሆንም ጠንከረን በመስራት  ግባችንን  አንመታለን
ብለዋል ።
አቶ ሰውነት ጨምረውም ጨዋታው በኬኒያ አልያም
በኡጋንዳ ቢካሄድ ኖሮ ለኢትዮጵያ  የተሻለ እንደነበር ነው የተናገሩት
።

 
 
 
 
 
No comments:
Post a Comment