ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በጉብኝታቸው መርኃግብር ውስጥ ኢትዮጵያንም ማካተት ነበረባቸው ሲሉ ለቪኦኤ አስተያየታቸውን የሰጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ የተለየ አስተያየት ያንፀባረቁም አሉ።
“ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በአፍሪካ የሚያደጉት ጉብኝት ሁለት መልክ የያዘ ነው” ብለዋል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ምኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ።
አምባሣደር ዲና ሙፍቲ ስለፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የአፍሪካ ጉብኝት
ለመሆኑ የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የአፍሪካ ጉብኝት በሦስቱ ሃገሮች /በሴኔጋል፣ በደቡብ አፍሪካና በታንዛኒያ/ እንዲሆን ለምንና እንዴት ተወሰነ? ዲፕሎማትና የውጭ ግንኙነቶች መምህር ዴቪድ ሺንትንታኔይሰጡናል፡፡
የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች አፍሪካን መርገጥ ከጀመሩ ሰባ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡
የመጀመሪያው ፍራንክሊን ሩዘቬልት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ምክንያት ከተባበሩት ኃይሎች አጋሮቻቸው ለመመካከር ነበር ካሣብላንካና ካይሮ የተገኙት፤ ከእርሣቸው በኋላ ጂሚ ካርተር፣ ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን፣ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ከፕሬዚዳንትነታቸው ዘመናት በኋላም በአፍሪካ የተለያዩ ሰብዓዊ ተግባራትን እያከናወኑ ነው፡፡
http://amharic.voanews.com
No comments:
Post a Comment