Wednesday, July 17, 2013

ዳንኤል አሁን ላይ ሆኖ ይህን ያስታውሳል


በሰለሞን ዮሃንስ


ዳንኤል አሁን ላይ ሆኖ ይህን ያስታው
“ለመጀመሪያ ግዜ ህልመ ሌሊት ሲታየኝ በጣም ነው የደነገጥኩት እንደነጋ ክኒሊክ ሄድኩ በሁኔታዬ የተገረመው ሀኪም እንድረጋጋ ከነገረኝ በኋላ ወላጆችህ ስለዚህ ጉዳይ እንዴት አልነገሩህም ሲል ጠየቀኝ እኔም በፍርሃት ነገሩ ለኔ አዲስ እንደሆነ እና ምን ዓይነት ህመም እንደሆነ ለማወቅ ነው የመጣሁት ስል ነገርኩት የሀኪሙን ግርምት እስካሁን አልረሳውም ጭንቅላቱን ነቅንቆ  ችግር እንደሌለውና የጉርምስና ምልክት እንደሆነ ነግሮ ሸኘኝ
የጉርምስና ዕድሜን ተከትሎ በሰውነታችን ላይ የታየው የአካልም ሆነ የስሜት ለውጥ ያላስደነገጠው ማን ይሆን ?
ይህስ ሊከሰት የሚችል እንደሆነ ቀድሞ ማን ነገረን ? ሁላችንም የራሳችን ገጠመኝ ይኖረናል ፡፡
ይህ መነሻ ይሁነን እንጂ ስለዚህ አይደለም የምናውራው  ስለወሲብ ሳንፈራ   በነጻነት የምናወራው ከማን ጋር ነው?
ይህን ጥያቄ  ለበርካታ የፕሮግራሙ ተከታታዮች በስልክ በአካል እና በፌስ ቡክ ላይ ጠይቄ ያገኘሁት መልስ በሙሉ ለማለት ይቻላል መልሱ ለምቀርበው ወይም ለምቀርባት ጓደኛዬ ነው የሚል ነበር፡፡
ወላጆቻችን የሚያውቁት ግን ለኛ ለልጆቻቸው በግለጽ የማያወሩን ይህ የወሲብና የፍቅር ጉዳይ “ነውር” የሆነበት ብዙ ምክንያት ሊኖረው ይችላል ለልጆች ግን የሁለት ባህሪ ባለቤት እንዲሆኑ አድርጓል ፡፡እቤት እቤት በጨዋ ሙድ መቀመጥ አና ውጭ የፈለጉትን ማድረግ ወሲብን ጨምሮ ፡፡
ስምንት የሚሆኑ ወንድና ሴቶች ጋር አውርተን ነበር “…እንዴ እንዴት ብዬ ነው የምናገረው” ብለዋል
ጨዋ ለመባል እንደሚያስመስሉ ሁሉ የነገሩኝ አሉ ፡፡ የወላጅ እና የልጅ ሀሳብ ለየቅል ነው፡፡ በድፍረት ስለፍቅር ና ወሲብ የሚያውሩ ወላጆች ስንት ይሆኑ ? ለልጆችስ ያለፍርሃት ስለስሜቶቻቸው መቼ ይሆን መነጋገር የሚችሉት  ?
ቢታኒያ እንዲህ ትላለች “አባቴ ሀርደኛ ነው እንኳንስ ሰለወሲብ ላወራ ቀርቶ ሌላ ጉዳይ ላይ ራሱ መነጋገር እፈራለሁ” 
ዳንኤል ደግሞ “ቀን ሃምሳ ቺክ ለከፍኩ በዬ ለመናገር ድፍረት ቢኖረኝ ኖሮ ሌላው ለኔ ቀላል ነው”  ይለናል
ካነጋገርኳቸው ልጆች ሰባቱ ሴክስ ጀምረዋል ወላጆቻቸው ግን ይህን ፈጽሞ አያውቁም ፡፡ ቢያውቁስ ? የኔ ጥያቄ ነበር
 “ያንጠለጥሉኛል” ከሚለው መልስ ጀምሮ  “በኔ ላይ ያለቸው እምነት ይቀንሳል”  “ላንነጋገር እንችላለን እና ሌሎችንም ብለውኛል፡፡
ወጣትነት ሁሉንም ነገር ለመሞከር የምንደፍርበት ወቅት ነው…..
በጓደኛም ግፊት ይሁን ለማወቅ ከመፈለግ የተነሳ የምንሞካክራት ነገር በዛ ትላለች ወሲብ መጀመር ሱስ ውስጥ መግባት አና የሀይለኝነት ጠባይ ይበዛብናል፡፡ ጋሽ ስብኃት እንዳለው “ወጣት ስትሆን……”
በርግጥ በኛ ሀገር ባህል እና የአኗኗር ስልት ዘሎ ስለፍቅር እና ወሲብ ማውራት ከባድ ነው፡፡ ስለዚህ ዝም ብለን እንቅር ወይሰ ከወለጆቻችን ጋር ቀላል በሆነ ዘዴ እንነጋገር ነው ጥያቄው
ለዚህ መፍትሄ አለው ያለችኝ ካፍሪካ ፕሌይ ቴራፒ ያገኘኋት ባለሙያ ናት “ ለልጆቻችን ስሜት ከምናሟላላቸው ሌሎች ነገሮች እኩል መጨነቅ አለብን” ትላለች፡፡ ወሬውን ለመጀመር ከባድ ቢሆንም በቀላሉ ውሎአቸውን በመጠየቅ ማለማመድ ይቻላል ነው የምትለው፡፡
ወሬው ታድያ በዕድሜ ደረጃቸው ቢሆን ይመረጣል ባይ ናት ባለሙያዋ፡፡
ወላጆችም እንግዶቼ ነበሩ፡፡ አቶ ሳሙኤል ልጃቸው ለሳቸው ሁሌም ልጅ ነች ስለወሲብም ሆነ ስለፍቅር ማውራት አይታሰብም ባይ ናቸው፡፡ የአቶ ሰሙኤል ልጅ 16 ዓመቷ ነው ምንአልባት ይላሉ ምናልባት 18ኛ ዓመቷ ላይ እጀምር ይሆናል ብለዋል፡፡
ሁለት የደርሱ ልጆች ያላት ወ/ሮ ሂሩት ግን ያላቸውን ተጋላጭነት ስታስብ ሁሌም ስጋት ያድርባታል እናም በምሳሌም ይሁን በሌላ ተዘዋዋሪ ዘዴ ስለውሲብና ተያያዥ ችግሮች ታወራለች በሳምንት አንዴም የቤተሰብ ቀን ስላለን ስሜቶቻቸውን መነሻ አድረገን እናውራለን ብላኛለች፡፡  
ዳንኤል በህልሙ የተከሰተው ህለመ ሌሊት በድንጋጤ ክሊኒክ ያስኬደው ያለምክንያት አይደለም፡፡   በወንድም ሆነ በሴት የመጀመረያ የስሜትም ሆነ የአካል ለውጥ ላይ  ማስረዳት ያለባቸው የመጀመሪያው ሰዎች  ወላጆች ናቸው፡፡  በዚህ  የተጀመረው ንግግር ስለ ፍቅርና ወሲብ ንግግር ሊያድግ ይችላል ..ጊዜው ይለያይ እንጂ ወላጆቻችንም ይህን ግዜ በየራሳቸው መንገድ አሳልፈውታልና ነው፡፡ እርግዝና  ከዚህም ሲከፋ ደግሞ የማይታረመው ስህተት ኤች አይ ቪ ሲከሰት ከቤት ማበረሩ አይንን ለማየት መጸየፉ መፍትሄ አይሆም፡፡ወላጆቻችን ስለወሲብ የሚያውቁት ግን ለኛ የማይነግሩን የሚለውን ፕሮግራም ብታዳምጡ ሙሉውን ሃሳብ ታገኛላችሁ፡፡




No comments:

Post a Comment