ዶክተር ዲላሚኒ ዙማ |
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2005 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፍሪካ ህብረት ሰሞኑን በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይ በኢትዮጵያና ግብፅ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ላይ መግለጫውን አውጥቷል ።
የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ዶክተር ዲላሚኒ ዙማ በመግለጫቸው እንዳሉትም ፥ የሁለቱ አገራት አለመግባባት ሊፈታ የሚችለው በድርድር ብቻ ነው ።
ግብፅ በቀኝ አገዛዝ ዘመን በተፈረሙና የአባይን ዉሃ 87 በመቶ እንድትጠቀም የሚያስችሏት ሁለት ስምምነቶች አሁንም ተጠብቀው እንዲፈፀሙ ትፈልጋለች ፡፡
ነገር ግን ከሶስት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያን ጨምሮ በርከት የሚሉ የተፋሰሱ አገራት የወንዙን አጠቃቀም አስመልክቶ በኡጋንዳ ኢንቴቤ አዲስ ስምምነት ተፈራርመዋል ፡፡
የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ኒኮሳዛና ዲላሚኒ ዙማ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ላይ ፥ በአባይ ወንዝ ላይ ያለው አለመግባባት አሁን ባለው ሁኔታ እንጂ በቅኝ አገዛዝ ወቅት በተደረሱ ስምምነቶች ሊዳኝ አይገባም ብለዋል።
ሁለቱ አገራት ወደ ንግግር እንዲመጡ ያሳሰቡት ሊቀመንበሯ ፥ ድርድሮች የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ሊያደርጉ እንደሚገባ ነው የጠቆሙት ፤ ሁለቱም አገራት ውሃው እንደሚያስፈልጋቸው በመግለፅ ።
http://www.fanabc.com
No comments:
Post a Comment