http://www.dw.de
የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን በመጪው
2014 ዓ-ም ብራዚል ውስጥ ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ውድድር ለመድረስ በሚደረገው የአፍሪቃ ማጣሪያ ትናንት
ደቡብ አፍሪቃን 2-1 በማሸነፍ የምድቡን አንደኝነት ማረጋገጡ አይዘነጋም።
ይሁንና የዓለም እግር ኳስ ፌደሬሺኖች ማሕበር ፊፋ ቡድኑ ከሣምንት በፊት ቦትሱዋና ውስጥ ባደረገው ግጥሚያ አንድ ያልተፈቀደለት ተጫዋቹን ሳያሰልፍ አልቀረም ሲል ዛሬ በከፈተው ምርመራ መልሶ ሶሥት ነጥቦች እንዳያጣ እያሰጋው ነው። እርግጥ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተሸናፊ ተደርጎ ቢፈረድበትም ምድቡን በሁለት ነጥቦች ልዩነት መምራቱን የሚቀጥል ሲሆን ከማዕከላዊት አፍሪቃ ሬፑብሊክ ጋር በሚያካሂደው የምድብ-አንድ መጨረሻ ግጥሚያ አሸንፎ ወደ ተከታዩ ዙር የማለፍ ትልቅ ዕድል አለው። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መቀጣት ደቡብ አፍሪቃን እንደገና ከሞት የሚመልስ ነው የሚሆነው። በጉዳዩ ዛሬ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ አቶ ሰውነት ቢሻውን በስልክ አነጋግረናል፤ ያድምጡ!

No comments:
Post a Comment