ኢትዮጵያ የኅዳሴን ግድብ ሥራ እንድታቆም ግብፅ እንደምትጠይቅ ተገለፀ ኢትዮጵያ “ፈጽሞ የማይታሰብ” ስትል መልስ ሰጥታለች፤ በሁለቱ የአባይ ተፋሰስ አገሮች መካከል የዲፕሎማሲ ትኩሣቱ አይሏል፡፡
የግብፅ ባለሥልጣናት ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የምትገነባውን የኅዳሴ ግድብ ግንባታ እንድታቆም ጠይቀዋል።
ኢትዮጵያ በበኩሏ ግንባታው የግብፅን የአባይ ውኃ ተጠቃሚነት እንደማይጎዳ በተደጋጋሚ በመግለፅ ግንባታውን ማቆም ፈጽሞ የማይታሰብ ነው ብላለች።
የግብፅ የቀድሞ የውኃ ሃብት ሚኒስትር ዶ/ር ሞሀመድ አላም ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “… በዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሠረት ኢትዮጵያ የግንባታዋን ዕቅድ ለኢትዮጵያ ማስታወቅ ነበረባት…” ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የምትገነባው የኅዳሴ ግድብ ወደ አምስት ቢሊዮን ዶላር የሚያስወጣ ሲሆን የግንባታ ወጭው ሙሉ በሙሉ የሚሸፈነው በኢትዮጵያዊያን እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
ግብፅና ሱዳን እ.ኤ.አ በ1959 የተፈራረሙት የአባይ ውሃ አጠቃቀም ስምምነት፤ 90 ከመቶ የሚሆነውን የአባይን ውኃ ለሁለቱ ሀገሮች 10 ከመቶውን ለትነት የመደበና ሰባቱ የአባይ ተፋሰስ የራስጌ ሃገሮችን ያለተጠቃሚነት ያስቀረ እንደሆነ የሚናገሩት ኢትዮጵያና ሌሎቹም ሃገሮች ሲቃወሙት መኖራቸው ይታወቃል።
ስለዚህም የተፋሰሱ የራስጌ ሃገሮች አገሮች ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ህዝባቸውን ለመመገብና ዕድገታቸውን ለማፋጠን የኃይል አቅርቦት በመሻታቸው በአባይ ወንዝ ላይ ፍትሃዊ የውኃ አጠቃቀም ስምምነት እንዲኖር ሲጠይቁ ቆይተዋል፡፡
ኤርትራና ደቡብ ሱዳን ከተጨመሩ በኋላ የተፋሰሱ ሃገሮች ቁጥር ከዘጠኝ ወደ አሥራ አንድ ማደጉ ይታወቃል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
http://amharic.voanews.comየግብፅ ባለሥልጣናት ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የምትገነባውን የኅዳሴ ግድብ ግንባታ እንድታቆም ጠይቀዋል።
ኢትዮጵያ በበኩሏ ግንባታው የግብፅን የአባይ ውኃ ተጠቃሚነት እንደማይጎዳ በተደጋጋሚ በመግለፅ ግንባታውን ማቆም ፈጽሞ የማይታሰብ ነው ብላለች።
የግብፅ የቀድሞ የውኃ ሃብት ሚኒስትር ዶ/ር ሞሀመድ አላም ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “… በዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሠረት ኢትዮጵያ የግንባታዋን ዕቅድ ለኢትዮጵያ ማስታወቅ ነበረባት…” ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲ እና የግብፅ የቀድሞ የውኃ ሃብት ሚኒስትር ዶ/ር አላም ሞሐመድ |
ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የምትገነባው የኅዳሴ ግድብ ወደ አምስት ቢሊዮን ዶላር የሚያስወጣ ሲሆን የግንባታ ወጭው ሙሉ በሙሉ የሚሸፈነው በኢትዮጵያዊያን እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
ግብፅና ሱዳን እ.ኤ.አ በ1959 የተፈራረሙት የአባይ ውሃ አጠቃቀም ስምምነት፤ 90 ከመቶ የሚሆነውን የአባይን ውኃ ለሁለቱ ሀገሮች 10 ከመቶውን ለትነት የመደበና ሰባቱ የአባይ ተፋሰስ የራስጌ ሃገሮችን ያለተጠቃሚነት ያስቀረ እንደሆነ የሚናገሩት ኢትዮጵያና ሌሎቹም ሃገሮች ሲቃወሙት መኖራቸው ይታወቃል።
ስለዚህም የተፋሰሱ የራስጌ ሃገሮች አገሮች ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ህዝባቸውን ለመመገብና ዕድገታቸውን ለማፋጠን የኃይል አቅርቦት በመሻታቸው በአባይ ወንዝ ላይ ፍትሃዊ የውኃ አጠቃቀም ስምምነት እንዲኖር ሲጠይቁ ቆይተዋል፡፡
ኤርትራና ደቡብ ሱዳን ከተጨመሩ በኋላ የተፋሰሱ ሃገሮች ቁጥር ከዘጠኝ ወደ አሥራ አንድ ማደጉ ይታወቃል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
No comments:
Post a Comment