Saturday, June 29, 2013

በካይሮ የኢትዩጲያ ስደተኞች ማህበር የአደጋ ጊዜ መከላከያ ግብረ ሃይል የወጣ መግለጫና ማስጠንቀቅያ

በ 30-6-2013 በሀገሪቱ ላይ በሚደረገው ሰለፍ ተነሳ ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ወጥተው በስደተኛው ላጭ ወጥተው በስደተኛው ላይ አደጋ ሊፈጥር እንደሚችል በቀጥታ የስደተኛው ጉዳይ የሚመለከተው የ UNHCR የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ ያወጣውን መግለጫ ማስነበባችን ይታወሳል። ይህ ባኢነዲህ እንዳለ ሌላኛው ከስደተኛው ጋር ግንኙነት ያለው የካሪታስ ቢሮ የችግሩን አደገኛነትና አሳሳቢነት በማመን የራሱነ መግለጫ ከማውጣቱም በላይ ቅድመሁኔታዎችን አስቀምጡአል በዚህም የተነሳ ማህበሩ ከስራ አስፈጳሚው ከሪጂናልና ከህብረተሰቡ ውሰጥ ተመረጡ አባላትን በማደራጀት ስደተኛውን ለመታደግ በዘመቻ መለክ የስራ እንቅስቃሴ ጀምርዋል።በዚህም መሰረት ስደተኛው በማንኛውም ጊዜና ቦታ ችግር ቢገጥመው በየሰፈሩ በተዋቀረው ግብረሃይል አማካኝነት በቀጥታ በተከፈተው ስልክ በመደወል አፋጣኝ እርዳታ የሚያገኝ ከመሆኑም በላይ ማህበርተኛው በዜጎች ላይ የደረሰውን ችግር በዚህ ስልክ በመደወል ማሳወቅ ይኖረበታል፦–መስር አል ጀዲዳ ለሚኖሩ……ቁጥር 1- ባልቻ-01001820761ቁጥር 2- ባልቻ- 01224935746መሃነድሲን ለሚኖሩ……..ቁጥር 1- ጎራው-01206239287ቁጥር 2-ጎራው-01151423038ማዓዲ ለሚኖሩ………………ቁጥር 1-ዛጎል-01153018903ቁጥር 2-ዛጎል-01001521972በመደወል አገልግሎት ማግኘት የሚቻል መሆኑን ሲያሳውቅ ስደተኛውም ሊመጠ ከሚችለው አደጋ እራሱን ይታደግ ዘንድ የሚቀጥሉትን ነጥቦች በስራ ላይ እንዲያውል ያሳስባል።-የካሪታስ ቢሮ ከ አረብ 28-06 2013 ጀምሮ ዝግ ነው-የ UNHCR የስደተኖች ቢሮ -ከ30-06- 2013 ጀምሮ ዝግ ነው-የ አሚራ ቢሮ ከ 30-06-2013 ጀምሮ ዝግ ነው-ሴንት አንደሮ ከ 30-06 2013 ጀምሮ ዝግ ነው-ተዳሙን ቢሮ 30-06-2013 ጀምሮ ዝግ ነውከዚህም በመነሳት ማንኛውም ኢትዩጲያዊ ስደተኛ፦- ከ 28-06-2013 ጀምሮ የግድ ካልሆነ በስተቀር ከቤት ባይወጣ ይመከራል- ከቤት መውጣት የግድ በሚሆንበት ጊዜ ከሀገሪቱ ዜጎች ጋር የሚያመሳስልአልባሳት መጠቀም- ይህ ችግር እልባት እስኪያገኝ ድረስ ስደተኛው የተለያዩ ዝግጅቶች ካሉት ወደሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ይመከራል- ስደተኛው በሚኖርበት አካባቢ ካሉት ሰዎች ጋርም ይሁን ከቤት አከራዩች ጋር ችግር ያለበት ከሆነ ለጊዜው ወደሌላ ሰፈር በመቀየር ይህን ክፉ ጊዜ እዲአሳልፍ ይመከራል- የ ሀገሪቱ ዜጎች በሚያደርጉት አካባቢን የመተበቅ ስራላይ በጥንቃቄ መሳተፍ- የግድ መንቀሳቀስ ያለብተ ስደተኛ የ UN ካርድ መያዝ አለበት- በስራ ቦታ ያሉ ስደተኞች እዚያ ያለው ሁኔታ አሰጊ እሰካልሆነ ድረስ እረፍት ባይወጡ ይመከራል- የውሀ የምግብ የመድሀኒት የመብራት የስልክና የ ኢነተርኔት ችግር ሊኖር ስለሚችል ለ-15 ቀን ያላነሰ አሰቤዛ ገዝቶ መጠበቅ የሰፈልጋለ- ልጆች ላላችው እነዲሁ አሰፈላጊው ዝግጅተ እንዲያረጉ ይመክራልማሳሰቢያ—የጦር ሃይሉ ባወጣው መግለጫ መሰረት ማንናውም የውጭ ዜጋ እሁድ በ-30-06-2013 ከቤት መውጣት የለበትም
   Source Ethiopian Observer

No comments:

Post a Comment