Wednesday, June 5, 2013

ሰሞኑን በአዲስ አበባ የሚፋቱ ባለትዳሮች መበርከት ከመኖሪያ ቤት ምዝገባ ጋር የሚያያዝ ይሆን ?


አዲስ አበባ፣ግንቦት 28 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለ10/90ና የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ምዝገባ ቅድመ ሁኔታ   ከተባሉት መካከል አዲስ የባንክ የቁጠባ ሂሳብ መክፈት አንዱ ነው ።
ይህን ዝግ የባንክ ሂሳብ ለመክፈት በባንኮች ከውተሮ  የተለየ  ሰልፍና ግርግር አምጥቷል ።
በሌላ በኩል  ተመዝጋቢዎች ባለትዳር መሆን አለመሆናቸውን ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ፥ እንደታዘብነው ለየብቻቸው  የመኖሪያ ቤት ለማግኘት ሲሉ ፍቺ ለመፈፀም ፍርድ ቤት የሚሄዱ ባለትዳሮች በርክተዋል የሚል ጥቆማ ደረሰን ።
የጥቆማውን አውነትነት ለማረጋገጥ ቅኝታችንን በበፌደራሉ ፍርድ ቤት በልደታና አራዳ ምድብ ችሎት ላይ አደረግን ።
በልደታ ምድብ ችሎት በሚያዚያ   ወር  የነበረው ፍቺ 150 ሲሆን ከግንቦትይ 1 እስከ 23 ድረስ በሂደት ላይ ሳይጨምር 122 ሆኗል፡፡
በአራዳ ምድብ ችሎት ደግሞ በሚያዚያ ወር ላይ 146 የነበረው የተፋቺዎች ቁጥር በተመሳሳይ ሁኔታ በሂደት ላይ ያሉትን ሳይጨምር 129 ደርሷል፡፡
በሂደት ላይ የሚገኙት የፍቺ ጥያቄዎችና ሌሎች ቀደም ሲል በህጋዊ መንገድ ትዳር ሳይመሰረቱ የኖሩ አፋቱን ሲሉ ህጉ አይፈቅድም ብለን የመለስናቸው ሲካተት ሰሞኑን በተለየ መልኩ ተፋቺ መብዛቱን እንደሚያመላክት ነው ፍርድ ቤቶቹ የነገሩን ።
ፍርድ ቤቶቹ ለዚህ ችግር መፍትሄ ሊሰጥ የሚችለው ጉዳዩን የሚያስፈፅመው አካል መሆኑን ይናገራሉ፡፡
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኤጀንሲ በበኩሉ ለጉዳዩ አዲስ አይደለሁም ከሶስት አመታት በፊት ባደረኩት የቤት እደላ ወቅት አጋጥሞኛል ፥በመሆኑም ጉዳዩ የሚጣራበት መላ ይዘጋጃል ብሏል ፡፡
በዚህ ማጭበርበር ተሳትፈው የሚገኙ ባለትዳሮችም በሚደርገው ማጣራትና ከህብረተሰቡ በሚገኘው ጥቆማ ከተደረሰባቸው የሚወሰድባቸው እርምጃ ሌሎች ቅጣቶችን ጨምሮ ከሁለት አንድ ያጣ ያደርጋቸዋል ብሏል ኤጀንሲው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ማንኛውም ወንጀል ከህብረተሰቡ የተደበቀ አይደለምና ፥ ህብረተሰቡም እንደዚህ አይነት የማጭበርበር ተግባሮችን  ለመንግስት በመጠቆም ትብብር እንዲያደርግም ኤጀንሲው ጥሪውን አቅርቧል፡፡
 በደመቀ ጌታቸው
http://www.fanabc.com 

No comments:

Post a Comment