Friday, January 24, 2014

The Missing Faces of Ethiopia’s Poor

Yenenesh Yigsaw (right) recovers from her latest reconstructive surgery with other Noma patients at a recuperation centre outside of Addis Ababa, Ethiopia's capital. Credit: Nick Ashdown/IPS
Gelegay's affability is notable because of what he's gone through. The 34-year-old farmer from a village in Ethiopia's Gojam region is a survivor of Noma, a rare flesh-eating infection that rots away the face.
When he was just two years old, Gelegay noticed black spots forming on his nose, which quickly spread downwards to his mouth. He received rudimentary treatment, but the diseased part of his face fell off.
Noma is only found amongst children (primary incidence is between the ages of one and four) in the poorest regions of the world, such as rural parts of sub-Saharan Africa and India. The World Health Organisation estimates there are 140,000 new cases globally each year.

Tuesday, January 14, 2014

“አለሁ ---- አልሞትኩም”

ረቡዕ ማታ በዛሚ 90.7 ኤፍ ኤም ሬዲዮ ላይ “አርቲስት ፈለቀ አበበ አረፈ” በሚል በስህተት በተነበበ ዜና እረፍት  ምክንያት አርቲስቱ፣ ቤተሰቦቹ፣ጓደኞቹና አድናቂዎቹ እስከ ሀሙስ እለት ተረብሸው ነበር፡፡ በርካቶች ዜናውን ባለማመን ነገሩን ለማረጋገጥ አርቲስት ፈለቀ አበበ ተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ ሲደውሉ ማምሸታቸውንና መዋላቸውን አርቲስቱ ገልጿል፡፡ በስህተት ከተሰራጨው ዜና እረፍት በኋላ አርቲስት ፈለቀ የማር ውሃ አበበ ስለተፈጠረበት ስሜትና አጠቃላይ ሁኔታ ከጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ ጋር  አጭር ቃለምልልስ አድርጓል፡፡

የሞትህን ዜና በምን ሁኔታ ሰማህ?

ረቡዕ ወደ ማታ ቤት ቁጭ ብዬ እየሰራሁ ሳለሁ፣ ባልተለመደ መልኩ ስልኮች በተከታታይ መደወል ጀመሩ፡፡ አስደንጋጭ ነበር፡፡ ብቻ የሆነ ነገር እንዳለ ያስታውቃል፡፡
ዜና እረፍትህን ሰምተው መደወላቸውን እንዴት አወቅህ?
አንዱን ጓደኛዬን በድፍረት ጠየቅሁት፡፡ ምክንያቱም በዚህ ፍጥነት በተከታታይ ሲደወል ለእኔ የተለመደ አይደለም፡፡  “ምንድን ነው ነገሩ? አካባቢው ላይ የተፈጠረ ነገር አለ እንዴ? ብዙ ሰው በተከታታይ እየደወለልኝ ነው” ብዬ ስጠይቅ፤“አይ ሞተሀል ተብሎ በሬዲዮ ተነግሮ ነው” ሲለኝ ክው ብዬ ደነገጥኩኝ፡፡ ደግሞ ያስታውቃል፤ አንዳንዶቹ ልክ ስልኬን አንስቼ “ሀሎ” ስላቸው ቶሎ ይዘጉታል። ብቻ መኖሬን ነው ማወቅ የሚፈልጉት፡፡ እንደዚህ ካደረጉት ውስጥ ጓደኛዬ አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ አንዱ ነው፡፡ አማኑኤል መሀሪ እንዲሁም ቤተሰቦቼም ድምፄን ሰምተው ብቻ ስልክ ዘግተዋል፡፡ ምክንያቱም ወደ ቤተሰቦቼም ይደወል ነበር፡፡ ከውጭ አገር ሁሉ የስልክ ጋጋታው ሊያቆም አልቻለም፡፡

ሲደውሉልህ የሰዎች ስሜት እንዴት ነበር?

በጣም ህመም የሆነብኝ እሱ ነው፤ በጣም የሚያለቅሱና ኡኡ የሚሉ ነበሩ (ለቅሶ…) በጣም ያሳዝናሉ፤ እኔም አብሬያቸው አለቅስ ነበር (ረጅም ለቅሶ)…
ሬዲዮ ጣቢያው ጋ አልደወልክም ?
ትንሽ ቆይቶ--- ከዛሚ 90.7 ኤፍ ኤም ደወሉልኝ፡፡ “በስህተት ነው ፈለቀ አበበ ሞተ ያልነው፤ የሞተው ግን አርቲስት ፈለቀ ጣሴ ነው፤ አንተ በጣም ታዋቂ ስለሆንክ ፈለቀ ስንል አፋችን ላይ የገባው የአንተ አባት ስም ነው” አሉኝ፡፡ ነገር ግን ሰው በጣም ያለቅሳል፤ በጣም ያሳዝናል፡፡

ይቅርታ ጠየቁ ወይስ----