Friday, February 27, 2015

ምንሊክ ……ጥቁር ሰው! The Battle of Adwa













The Battle of Adwa (also known as Adowa, or sometimes by the Italian name Adua) was fought on 1 March 1896 between the Ethiopian Empire and the Kingdom of Italy near the town of Adwa, Ethiopia, in Tigray. It was the climactic battle of the First Italo-Ethiopian War, securing Ethiopian sovereignty.
As the 20th century approached, most of Africa had been carved up among the European powers. The two independent exceptions were the young Republic of Liberia on the west coast of the continent and the Ethiopian Empire in the strategicHorn of Africa. The newly unified Kingdom of Italy was a relative newcomer to the colonial scramble for Africa. Italy had two recently obtained African territories: Eritrea and Somaliland. Both were near Ethiopia on the Horn of Africa and both were impoverished. Italy sought to improve its position in Africa by conquering Ethiopia and joining it with its two territories.

Wednesday, February 25, 2015

ከአባት አርበኛ ጋር አዝናኝ ቃለምልልስ ናፍቆት ዮሴፍ

የ95 ዓመት አባት አርበኛ ናቸው፡፡ ያልዘመቱበት የጦር አውድማ የለም። በዚህ ዕድሜያቸው ከ70 ዓመት በፊት የተደረጉ ጦርነቶችን ከእነ ዓመተምህረታቸው ያስታውሳሉ፡፡ 
ባለፈው ሳምንት በኢኮኖሚና ንግድ አምድ ላይ ቃለምልልስ የተደረገላቸው “የባላገሩ አስጐብኚ ድርጅት” ባለቤት፣ አባት አርበኞችን ወደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ወስዶ የማስጐብኘት ሃሳብ የመጣላቸው በእኚህ አዛውንት ጥያቄ መሆኑን ገልፀውልናል፡፡ 
የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛዋ ናፍቆት ዮሴፍ ከእኚህ የዕድሜ ባለፀጋ አባት ጋር ማራኪና አዝናኝ ቃለምልልስ አድርጋለች። እነሆ:-



ስምዎትን ያስተዋውቁኝ አባት…
ሃምሳ አለቃ ደምሴ ፀጋዬ እባላለሁ፡፡ ትውልድና እድገቴ ወሎና ጎንደር ነው፡፡ በአንድ ጎን ደባት ገብርኤል ነኝ፡፡ በሌላ ጎኔ ደግሞ ወሎ ውስጥ የጁ እና ላስታ ነው እድገቴ፡፡ ጠቅለል ስታደርጊው ዘር ሃረጌ ከወሎ እና ከጎንደር ይመዘዛል ማለት ነው፡፡ 
እስቲ ስለልጅነት ያጫውቱኝ?
እንዴ! የአስተዳደጌ ሁኔታማ ምን ይወራል። የተወለድኩት በ1911 ዓ.ም ታህሳስ 3 ቀን ነው፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምረሽ እድሜዬን ማስላት ትችያለሽ፡፡ ጠላታችን ጣሊያን መጥቶ አባቶቻችን ሲዘምቱ የ18 ዓመት አፍላ ጎረምሳ ነበርኩኝ፤ በ1928 ዓ.ም ማለት ነው፡፡ አባቴ በውጊያው ቆስሎ ነበር ከዘመቻው የተመለሰው፡፡ 
የት ቦታ አባትዎ እንደቆሰሉ አልነገሩዎትም?
ነግሮኛል! ማይጨው ላይ ነው የተመታው፡፡ የዘመተው ከደጃዝማች አድማሱ ብሩ ጋር መሆኑንም አጫውቶኛል፡፡ ደጃዝማቹ እዚያው በውጊያው ሲሞቱ፣ አባቴ ግን ቆስሎ መጣ፡፡ የማስታውሰው እኔ የ19 ዓመት ወጣት ስለነበርኩ፣ አባቴ ውጊያ ሲሄድ የእርሻውን ስራ እኔ እሸፍን ነበር፡፡ አባቴ ከውጊያ የመጣ ቀንም ሞፈርና ቀንበሬን አነባብሬ እርሻ ወርጄ ማሽላ ስዘራ ነበር የዋልኩት፡፡ እነሱ ሲመጡ ጥይቱ እንደ ማሽላ ቆሎ… ጣ  ጣ   ጣ  ጣ ይላል፡፡ ምንድን ነው ነገሩ ብዬ ስጠይቅ፤ “አባትሽ መጣ” አሉኝ፤ አንቺ ነበር የሚሉኝ፡፡ 
ለምንድነው አንቺ የሚልዎት?
ምክንያቱ በግልፅ አይገባኝም፡፡ ስገምት ግን ስራመድ ከእግሬ እንደ ሴት ፈጠን እላለሁ፡፡ ለዚያ ይመስለኛል፡፡ 
ከዚያስ?

Monday, February 2, 2015

‹‹ልጅነቴ በሙዚቃ ተጣጥሞ አልፏል›› ፀሐይ ዮሐንስ

 ተጻፈ በ  
የፀሐይ ዮሐንስ
 ‹‹ማንበብና መጻፍ ዋናው ቁም ነገር፤ ከሕይወቴ ጐሎ እሸበር ጀመር›› የሚለው ስንኝ የብዙዎች ትዝታ ነው፡፡
በጊዜው በመሠረተ ትምህርት ዘመቻ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደነበረውም ይታመናል፡፡ ‹‹ሳብ ሳም››፣ ‹‹ተባለ እንዴ›› እና ‹‹ያላንቺማ›› የፀሐዬ (ብዙዎች እንደሚጠሩት) ስም ከሚነሳባቸው ዘፈኖች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በተመሳሳይ ስለ ሀገር ያዜማቸውም የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ፀሐዬ ‹‹የኔታ›› የተሰኘ አልበም በቅርቡ ለቋል፡፡ አልበሙንና አጠቃላይ የሙዚቃ ሕይወቱን በሚመለከትምሕረተሥላሴ መኰንን ከፀሐዬ ዮሐንስ ጋር ቆይታ አድርጋለች፡፡  
ሪፖርተር፡- ከመታወቅህ አስቀድሞ የሙዚቃ ሕይወትህ ምን ይመስል ነበር?
ፀሐይ፡- ጃንሜዳ አካባቢ መኖሬ ወደ ሙዚቃ ለመግባቴ ትልቁ ምክንያት ይመስለኛል፡፡ የልጅነቴን ተሰጥኦ እዛ ነው ያዳበርኩት፡፡ በምንነጋገርበት በዚህ የጥምቀት ሰሞን ብዙ ትዝታ አለኝ፡፡ ጥምቀት ለሙዚቃ ፍቅሬ መንገድ የከፈተ ነው፡፡ ያደግኩበትም ግቢ ጃንሜዳ አጠገብ ባለው ሙዚቀኛ ግቢ ነው፡፡ ጥላሁን፣ መሐሙድና ብዙነሽ የነበሩበት ክብር ዘበኛ ኦርኬስትራ ትልቁን ሚና ተጫውቷል፡፡ ጠዋት ደብተር ይዤ ሄጄ እዛ እውላለሁ፡፡ ክብር ዘበኛ ባልሠራም የክብር ዘበኛ ልጅ ስለሆንኩኝ ልጅነቴ በሙዚቃ ተጣጥሞ አልፏል፡፡ 
ሪፖርተር፡- ድምፃዊነትን ሙያዬ ብለህ ‹‹በርታ ዘመዴ››ን ከተጫወትክ በኋላስ? 
ፀሐይ፡- ያኔ ዜማ ማውጣት ጀመርኩ፡፡ ‹‹ማንበብና መጻፍ›› የኔ ዜማ ነው፡፡ አቶ ተስፋዬ ለማ አምባሳደር ቴአትርን ባቋቋሙበት ጊዜ በ1970 ዓ.ም. ከጓደኞቼ ጋር የመጀመሪያ ቅጥሬን አምባሳደር አደረግኩ፡፡ ከዛ በፊት ከክብር ዘበኛ ጋር ለዕድገት በኅብረት ዘመቻ ‹‹በርታ ዘመዴ ዘማቹ ጓዴ››ን ከሒሩት በቀለ ልጅ ጋር ሆነን ሠርተናል፡፡ ከዛ በኋላ አሻራዬ ያረፈባቸው 14 አልበሞች አሉኝ፡፡ 
ሪፖርተር፡- የመጀመሪያ አልበምህ እንዴት ነበር? 
ፀሐይ፡- ሙዚቃ ቤቶች ፕሮዲውስ ያደርጉ ስለነበር ልምድ ያለው ሰው ይፈልጋሉ፡፡ በዛ ወቅት ገና ልጅ ነኝ፡፡ ስሜት እንጂ ልምድ የለኝም፤ ስሜቴን ወደ ተግባር ለመቀየር ገንዘብ ስለሚያስወጣ ፕሮዲውሰሩ ይቸገራል፡፡ እንደ ምንም የመጀመሪያው ካሴት በሱፐር ሶኒክ ሙዚቃ ቤት አሳታሚነት ተሠራ፡፡ ጥሩ እየተሸጠ እያለ በአጋጣሚ እነ መሐሙድ አህመድና ውብሸት ፍስሐ ወደ ኤሜሪካ ከዋልያስ ባንድ ጋር ሄደው በኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ ታጅበው ‹‹ማለዳ ማለዳ›› ያለበትን ካሴት አወጡ፡፡ ካሴቱ የእኔን ሸፈነውና ብዙ ሳይደመጥ አለፈ፡፡ በዓመቱ በንዴት ‹‹ፍንጭቷ››ን ሠራሁ፡፡ ‹‹ፍንጭቷ››ን ይዤ ስወጣ ፀሐዬ ዮሐንስ የሚለው ስምም ተገኘ፡፡ 
ሪፖርተር፡- ትንሹና ከፍተኛውስ ክፍያ ስንት ነው? 
ፀሐይ፡- ያልተለመደ ዘዬና ድምፅ ይዤ ስለመጣሁ በሽያጭ ‹‹ፍንጭቷ›› በጣም ኃይለኛ ነበር፡፡ ‹‹ሳብ ሳም››፣ ‹‹ተባለ እንዴ›› እና ‹‹ያላንቺማ›› በጣም ጥሩ ሥራዎች ነበሩ፡፡ የመጀመሪያ ክፍያዬ 3,000 ብር ነበር፡፡ እንደ ጀማሪና በወቅቱ ገንዘቡ ከነበረው ዋጋ አንፃር ትልቅ ነበር፡፡ የ300,000 ሺሕ ብር ያህል አቅም ነበረው፡፡ የመጀመሪያ ካሴት ስም ማግኛ ስለሆነ ከክፍያ ይልቅ ስም ማግኘቱ ላይ አተኩሬ ነበር፡፡ 
ጥበብን በገንዘብ መለካት አስቸጋሪ ነው፡፡ በተለይ በእኛ ሀገር በሥራውና በተሸጠው መጠን አይከፈልም፡፡ መልካም ሥራ በመሥራት መልካም ስም ነው የሚተርፈው፡፡ በ‹‹ተባለ እንዴ›› ጊዜ ክፍያው 100,000 ሺሕ ብርም ደርሶ ነበር፡፡ ከ‹‹ተባለ እንዴ›› በኋላ የካሴት ሥራ የተበላሸበት ዘመን ነው፡፡ ሰው ሸጦ የሚያተርፍበት ጊዜ አልነበረም፡፡ ኮምፒዩተር መጣና በደቂቃ ሁሉም ሰው የሚቀዳበት ደረጃ ደረሰ፡፡ ሲዲ ከመምጣቱ በፊት ሽያጭ ጥሩ ነበር፤ ከፍተኛ የገቢ ምንጭም ነበር፡፡ ኦሪጅናል ካሴት 13 ብር ይሸጥ ነበር፡፡ ለማባዛት ባዶ ካሴት አምስት ብር ማስቀጃ ሦስት ብር ነበር፡፡ አምስት ብር ጨምሮ ኦሪጅናል መግዛት ስለሚመረጥ ገበያ ነበር፡፡ ዛሬ በአንድ ፍላሽ እስከ 500 ዘፈን ስለሚያዝ ኦሪጅናል የሚገዛ የለም፡፡ አቁሞ የሚያስኬደን ከኮንሰርት የሚገኝ ገንዘብ ነው እንጂ ዛሬ የሚሠራው ለነገ አያበረታታም፡፡ ጥበቡ እየሞተ ይመስለኛል፡፡ ባወጣሁት ልክ ካላገኘሁ የመሥራት አቅሜ ይዳከማል፡፡ ዛሬ እኔ ነገ ደግሞ ሌላው ከዘርፉ ይወጣል፡፡ በ‹‹የኔታ›› አልበም ብዙ ነው ያወጣሁት፡፡ የሚመጣውና የሚገኘው ተመጣጣኝ ካልሆነ ነገ ለጥበብ ብዬ ለፍቼ ልሠራ አልችልም፡፡ አልበሙ በሙሉ ባንድ ነው የተሠራው