Tuesday, September 12, 2017

ማር እስከ ጧፍ (ፍቅር እስከ መቃብር)


የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የሚጀምረው ስንት ሰዓት ላይ ነው?



በዲያቆን ዳንኤል ክብረት




ዓርብ ለቅዳሜ ምሽት፣ጳጉሜን አምስት 2002 / ማታ በኢትየጵያ ቴሌቭዥን ይተላለፍ የነበረውን የአዲስ ዓመት ዋዜማ እያየሁነበር፡፡ ከአሜሪካ የገባሁት በዚያው ቀን ነበርና ዕንቅልፌ ሊስተካከልልኝ ስላልቻ በደንብ ነበር የተከታተልኩት፡፡ እኩለ ሌሊት ሊደርስ ሲል ግን አንድ አሳዛኝ ነገር ተከሰተ፡፡ የማከብራቸው አርቲስቶች ወደ መድረኩ ተሰባስበው ወጡና በዚያች ታሪካዊት ቀን ታሪካዊውን ስሕተት ሰሩት፡፡ እኩለ ሌሊት ስድስት ሰዓት ሊሆን ሽርፍራፊ ሰኮንዶች ሲቀሩ «አዲሱ ዓመት ሊገባ ስለሆነ እንቁጠር» አሉና ወደ ኋላ አሥር፣ ዘጠኝ፣ ስምንት፣እያሉ እስከ ዜሮ ቆጠሩ፡፡ 
.
ከዚያም ከምሽቱ ስድስት ሰዓት ላይ አዲሱ ዓመት ገባ ብለው አወጁ፡፡ «የሊቃውንቱ ስሕተት እድሜ ሲያገኝ ሕግ ይሆናል» ይላሉ፡፡ በጥንት ጊዜ አውስትራልያ የገባ አንድ አውሮፓዊ አይቷት የማያውቅ አዲስ ፍጡር ያይና የሀገሬውን ነዋሪ «ይህቺ እንስሳ ማን ትባላለችብሎ ይጠይቀዋል፡፡ ያም የሀገሩ ነዋሪ «ካንጋሮ» ብሎ መለሰለት፡፡ ያም ሰው «ካንጋሮ» የምትባል እንስሳ አገኘሁ ብሎ ለዓለም ተናገረ፡፡ በሀገሬው ቋንቋ ግን «ካንጋሮ» ማለት «አላውቅም» ማለት ነበር፡፡ አንድ ሞኝ የተከለውን አምሳ ሊቃውንት አይነቅሉትም እንዲሉ ይሄው ስሟ ሆኖ ቀረ፡፡

“መሰንቆ እና ብትር” ከበዕውቀቱ ሥዩም

መሰንቆ እና ብትር (ወግ)

መሰንቆ እና ብትር
ከበዕውቀቱ ሥዩም
.
አያችሁት ብያ፣ የኛን እብድ፤
አምስት ጋሞች ይዞ፣ ጉራምባ ሲወርድ …”
አዝማሪ ጣፋጭ [1845 .]
.
የዳሞቱ መስፍን ደጃዝማች ጎሹ እና የቋራው ፋኖ ደጃዝማች ካሳ በኅዳር 19 1845 . ጉራምባ ላይ ጦርነት ገጠሙ። ካሳ፣ ከጥቂት ታማኝ ጭፍሮቻቸው ፊት ተሰልፈዋል። ጎሹም፣ በተለመደው የጀብድ መንገድ ከሰራዊታቸው ፊት ለፊት ቀድመው፣ ሲዋጉና ሲያዋጉ ውለዋል። ውጊያው እንደተፋፋመ፣ ደጃች ጎሹ በጥይት ተመትተው ወደቁ። የመሪውን መውደቅ እንደተረዳ የዳሞት ጦር ፀንቶ መመከት ተሳነው። ወዲያው የንቧይ ፒራሚድሆነ።ያለቀው አልቆቀሪው ተማረከ። 
ከምርኮኞች አንዱ፣ አዝማሪው ጣፋጭ ነበር። ጣፋጭ፣ የደጃች ጎሹ አዝማሪ ስለነበር በብዙ ጦር ሜዳ ላይ ውሏል። በጌታው ጠላት እጅ ሲወድቅም የመጀመሪያው አይደለም። በራስ ይማም ዘመንም እንዲሁ፣ ደጃዝማች ማጠንቱ የተባለ መስፍን ደጃዝማች ጎሹን ድል በነሳ ጊዜ፣ ከጌታው ጋር ተማርኮ ነበር።
ይሁን እንጂ ያኔ ዝንቡን እሽ ያለው አልነበረም። ጣፋጭ፣ የደጃች ማጠንቱ ምርኮኛ ቢሆንም፣ የእግር ብረት አልገባበትም። እንዲያውም፣ በድል አድራጊው አዳራሽ ውስጥ ያሻውን ከማንጎራጎር አልተከለከለም ነበር። በወቅቱም፣ አዝማሪው ጣፋጭ ይህንን ገላጋይ ዝማሬ አቅርቦ ነበር፤
አስረህ አንድ አትግደል፣ ደጃዝማች ማጠንቱ 
ለጀብዱ እንደሆነ፣ ይበቃል ስምንቱ።