Tuesday, May 21, 2013

ያገር ልጅ

  በሰለሞን ዮሀንስ
ያገር ልጅ የተጻፈው በሪቻርድ ራይት ነው፡፡

 ሣህለ ሥላሴ ብርሃን ማሪያም ተርጉመውታል
የታተመው በ 1995 ዓ.ም ነው…ርዕሱ ይማርክገኛል  …ቅርበት አለው ….ጥሪም ይመስላል


መጽሃፍ አዙዋሪ ላይ አየሁትና ዋጋውን ብጠይቀው  80 ብር አለኝ …የጀርባው ዋጋ 18፡70 ይላል
አሁን ኮ ገበያ ላይ የለም …ውሰደው …. በጣም ዐሪፍ መጽሃፍ ነው እያለ  …አንዴ ለቀቀብኝ …
አይ እለፈኝ አልኩትና…ተለያየን….ካንድ ወር በኋላ ይመስለኛል አራት ኪሎ አካባቢ በተዘጋጀ የመጽሃፍ ዐውደ ርዕይ
ይህንኑ ያገር ልጅን በ 20 ብር አፈስኩት፡፡


የደራሲው መግቢያው እንዲህ ይላል …
.“ የሪቻርድ ራይት Native Son ወይም ያገር ልጅ ለመዝናናት ታስቦ የሚነበብ መጽሃፍ አይደለም አንባቢው ይህን  ሀቅ
በቅድሚያ ቢያውቀው እወዳለሁ…. ” ሲሉ ያስጠነቅቁና ወረድ ብለው ደግሞ
“ሃይል አለው…ማግኔት ወይም የመሬት ሥበት የመሰለ ሃይል ፡፡ በአጉል ልማድ ልማድ የማምን ሰው ብሆን ኖር ድርሰቱ
ምትሃተዊ ነው ደራሲውም ምትሃተኛ ነው ባልኩ ነበር….ነገር ግን በዚህ አይነት ልማዳዊ ዕሳቤ አላምንም ” ይሉናል


የመጽኀፍ ጀርባ ላይ የሚጻፉ አስተያየቶች  ስንቴ ሸውደወናል….
አንዳች  ሃይል ያለው….ከትክክለኛ የህይወት ምንጭ የተቀዳ….. አንዴ ከገለጡት የማይከድኑት……..በዙ ብዙ….
ተብሎላቸው …ለብስጭት የዳረጉን መጻህፍትን     እናንተው ቁጠሯቸው…


…ለአዳዲስ ጸሀፍትም ሆነ አስተያየት ለመጻፍ ለሚጋበዙ ሓሲያን  ደራሲያን እና ዝነኛ ሰዎች ጥሩ መልዕክት የያዘ ይመስላል 
የአንጋፋው ደራና ተርጉዋሚ ሣህለ ስላሴ ብርሃነ ማሪያም አስተያየት……
አናውራበት….

No comments:

Post a Comment