Friday, July 5, 2013

በልጅነት የልጅ አባት



ተስፋሁን 21 ዓመቱ ነው፡፡ከፍቅረኛ  ጋር አንድ ሰፈር ናቸው የሚማሩትም አንድ ትምህርት ቤት ነው ይህ ደግሞ የበለጠ እነዲግባቡ አስቸሎዋቸዋል፡፡አብረው ይሄዳሉ አብረው ይመለሳሉ…ካፌ ዘና ይላሉ በቃ አሪፍ የፍቅር ግዜ ነው የሚያሳልፉት  ፡፡ታዲያ ተስፋሁን ይህ ጅምር ፍቅር እነዲጠነክር እና አንዲጸና ሴክስ ማድርግ ፈልጓል “ወሲብ ፍቅርን ያጠነክራል” የሚል የተለመደ ሀሳብ አለው፡፡  መቼ እና የት ማድረግ እንዳለበት ሁሉ ወስኗል ለዚህ ደግሞ ከእህቱ ጋረ ብቻ ስለሚኖር የት ሚለው ጥያቄ በቀላሉ ተመልሶለታል ምክንያቱም  የራሱ ክላስ አለውና  ሌላው ትልቁ ጉዳይ ፍቅረኛውን ማሳመን ነው ፡፡ ይህም ከተከታታይ ጨዋታ በኋላ ተሳክቶለታል፡፡ወሲብ ያረጉበትን ቀን ሲያስታውስ በአጭር ቃል እንዲህ ብሏል “በጣም ስለምወዳት እና ስለማምናት እኔ ክላስ ሴክስ አረግን”  
የመጀመሪያው ግነኙነትን  ላይ ኮንደም መጠቀሙን ያስተወሳል ከዛ በኋላ ግን ተላመድን በሚል ሰበብ ምንም አይንት መከላከያ አልተጠቀሙም ፡፡ሞቅ ያለውና በወሲብ የታጀበው የተስፋሁን ፍቅር ግን በዚሁ አልቀጠለም አንድ ቀን ፍቅረኛው አጥብቃ እንደምትፈለገው ትነግረውና ይገናኛሉ “ግን ትወደኛለህ” ትለዋለች እየደጋገመች በዚህ አዲስ ሁኔታዋ ግራ የተገባው ተስፋሁን ምን አንደሆነች ሲጠይቃት በፍርሃት እና በእንባ  ታጅባ የወር አበባዋ ከቀኑ እንደዘገየ  ትነግረዋለች፡፡ ይህ ለትስፋሁን አስደነጋጭ ነበር፡፡ ለረጅም ሰዓት ከዝምታው ሲመለስ እያለቀስች ነው ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ የገባው ተስፋሁን አባብሎ ወደቤትዋ ሲሸኛት ለማንም እንዳትናገር በማስጠንቀቅ ነበር በኋላ ላይ እርግዝናዋ በርግጥም በምርምራ ተረጋግጦአል ፡፡
ከዚህ በኋላ የሁለቱም ህይወት ተቀየረ እሷ በዚህ ክስተት ከቤት ተጣልታ እሱ ጋር ገባች ሆድዋ እየገፋ ሲመጣ ትምህርተዋን ተወች …የሱ ጭንቀት ደሞ ልክ አልነበረውም…አሁን ተውልዶስ እንዴት ነው የሚኮነው? ማሳደጉስ?   አባትነት ? …ብዙ ነገር ያስጨንቀዋል ስለወደፊቱ በጣም ያስባል እሱ ራሱ ተማሪ የእህቱ ጥገኛ ነው  ብዙ ጭንቀት በውስጡ ይተረማመሳል ከፍቅረኛው እርግዝና በኋላ እያንዳንዷ ቀን ለሰስፋሁን ጭንቀት ያዘለች ነበረች ጥያቄዎቹ በአዕምሮው እየተመላለሱ እረፍተ ይነሱታል ፡፡አባትንት ? ማሳደግ ? ገንዘብ ? ብዙ ነገር አሁን ባለበት እድሜ ለመመለስ የሚያስቸግሩ፡፡
 ቀኑ  መድረሱ አልቀርም ገና በልጅነቱ ልጅ ወለደ“ አባትንት ከባድ ነው” የሚለውው ተሰፋሁን“ ሀይለኛ ፍቅር ላይ ስለነብረኩ ምንም አይነት መከላያ ለመሞከር እንኳ አልታየኝም” ይላል ምንም አንኩዋ በሰላም ልጁ ብትወለድም የተስፋሁን ፍቅረኛ ከ ወሊድ በኋላ ጥቂት ቆይታ ለተሻለ ስራ አረብ ሀገር ተሰዳለች ተስፋሁንም ከሷ ቤተሰብ ጋር ስለተስማማ ልጁን ወስደው እነዲያሳድጉለት ሰቷቸዋል  ግን ተስፋሁን ደጋግሞ ይናገራል አባትነት እጅግ ከባድ እንደሆነና በቂ የስነልቦና የገንዘብ ዝግጅት እነደሚያስፈልገው፡፡ መሉን የሬዲዮ ፕሮግራም  ያድምጡት

No comments:

Post a Comment