Friday, May 24, 2013

ያልተንበረከኩ መንፈሶች





ቢኒያም ውብሸት





ከልጅነት እስከ እርጅና  ህይወት ትግል ነው፡፡ መማር ትግል ነው፤ ከሚወዱትን ሰው ጋር በፍቅር አብሮመቀጠል ትግል ነው፤ ከቤተሰብ ጋር ተግባብቶ መኖር ትግል ነው፤ ስራ ተቀጥሮ መኖር ትግል ነው ፤ ማንነትን ፈልጎ ማግኘት ትግልነው፤የህይወት ግብን ማሳካት ትግል ነው፤ ….. ትግል ያልሆነ የህይወት ክፍል አለ ማለት አይቻልም፡፡
እነዚህ ህይወት ለሁሉምሰው ያስቀመጠቻችው የቤት ስራዎች ናቸው፡፡ እዚህ ላይ አካል ጉዳተኝነት ሲጨመር ፈተናው ከበድ ይላል፡፡
ስለ አካልጉዳተኝነትእና ህይወት ፕሮግራም ከመስራቴ በፊት የ15 ደቂቃ ሙከራ አድርጌ ነበር፡፡ አይኔን በጨርቅ በመሸፈን ከዚህ በፊት በቀላሉ እሰራቸውየነበሩ ነገሮችን ልስራ በማለት መተጣጠብ፤ ልብስ መቀየር የመሳሰሉትን ነበር ለመስራት የሞከርኩት፡፡
እጅግ በጣም ከባድ ነገርሆኖ ነው ያገኘሁት፡፡ ሽንት ቤት ለመሄድ ከበር ጋር ተጋጭቻለሁ፡፡ የጥርስ ሳሙና ለማግኘት መደርደሪያ ላይ የነበሩ የሎሽን እቃዎች፤የጥርስ ብሩሾች፤ ተዘርግፈው የተወሰኑ ብልቃጦችን ሰብሬያለሁ፡፡ በመዳሰስልብስ ለመቀየር ፈልጌ የትኛው ልብስ እንደሆነ ለማወቅ በጣምአስቸጋሪ ሆኖብኛል፡፡
የምራመደው በፍርሃትነበር እቤቴ እንዲህ የፈራሁ ውጪስ ብወጣስ …. አካል ጉዳተኛ ብሆን እውነት ሰርቼ እኖራለሁ ያሰኛል ክብደቱ፡፡ በተለይ እንደኛበየቀኑ ጉድጓድ በየቦታው በሚቆፈርበት፤ አሽከርካሪ እንደፈለገ በሚከንፍበት፤ ሰው እየሮጠ በሚገፋህ አገር አይነስውር ሆኖ መግባትመውጣት ልዩ ጥንካሬ የሚጠይቅ ስራ ነው፡፡

"አካል ጉዳተኝነትለአካልጉዳተኛ እውነታ ጉዳት ለሌለው ደግሞ ሊያጋጥም የሚችል ሁኔታ ነው፡፡" የሚል አባባል ትዝ አለኝ፡፡
ታዲያ በዚህ ስሜት ሆኜነው ሁለቱን ባለታሪኮቼን ያገኘሃቸው፡፡ ዊልቸር ተጠቃሚው የሚኒልክ ተማሪ እና ነጋዴው ታመነን እንዱ ሲሆን የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲየህግ ተማሪ የሆነችውን አይነስውራን አበባ ደግሞ ሌላዋ ባለታሪክ ነች፡፡ ከሁለቱም ጋር መቆየት ሃይል እንደመታጠቅ ነው፡፡
የታመነን የመንፈስ ጥንካሬእና የማንም ተረጂ መሆን አለመፈለግ ስሰማ አካል ጉዳተኛ ሳይሆኑ የሰው እጅ እያዩ የሚኖሩ ብዙ ልጆችን ነው ያስታወሰኝ፡፡ ከዚህበፊት ቅፈላ ላይ ስንሰራ ባለታሪካችን የነበረው ታሪኩ ነበር ፊቴ ድቅን ያለው፡፡
ታመነ ካለኝ ነገር ሁሉአይምሮዬ ላይ የሚያቃጭለው የሰውነታችን ሞተር ጭንቅላታችን እንጂ እግራችን አይደለም ያለው ነው፡፡ ጥንካሬው ያስቀናል፡፡
ከአበባ ጋር ለመጀመሪያግዜ የተቀጣጠርነው በግ ተራ ነበር፡፡ በጣም የሚያምር ቀይ ረጅም ቀሚስ ከጥቁር ታኮ ጫማ ጋር አድርጋ ረዘም ያለውን ጸጉራን እየነሰነሰችያለምርኩዝ ያለ ጥቁር መነጽር ስትመጣ አይነስውር እንደሆነች ማወቅ አይቻልም፡፡
ከሰላምታ እያወራን ስንሄድከኋላ የሚመጡ ከፊት የሚሄዱ ልጆች ሳያዩዋት ስማቸውን እየጠራች ሰላም ስትል አጃኢብ ያሰኛል፡፡ ከአበባ በጣም ደስ የሚለው ነገርሳቅ እና ጨዋታዋ ነው፡፡ አበባን ያገናኘችኝ ልጅ ስትገልጻት "ቀውጢ" ነች ነበር ያለችኝ፡፡ ለአካባቢው ድምቀትነች፡፡ ገንጠል ብለው መጥተው ሰላም የሚላትን ልጆች በቀልድ እና በነገር ጠቆም እያደረገች በሳቅ ትገላቸው ነበር፡፡
ብዙ ግዜ ስለአካል ጉዳተኛስናስብ የሚመጣልን
 ተስፋ የቆረጠ፤ ለችግሩ ሁሉ አካል ጉዳተኝነቱ ላይ የሚያሳብብ፤ እና የሚታዘንለትአይነት ሰው ነው፡፡
ከነሱ ጋር በመቆየቴየተማርኩት ነገር አካል ጉዳተኞች ስሜት እንዳላቸው፤ ለሌላው እንደሚያዝኑ፤ ራእይ እንዳላቸው፤ እሱንም ለማሳካት ከእኛ በላቀ ሁኔታየሚያጋጥማቸውን እየታገሉ እንደሆነ፤ ለሃገራቸው ለቤተሰባቸው እንደሚያስቡ እና ተጫዋች እና ቀልደኞችም እንደሆኑ ነው ያየሁት፡፡
https://www.facebook.com/BiniyamWubishetDaguYouthMedi 


No comments:

Post a Comment