Friday, June 21, 2013

ደቡብ ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ለመገንባት 16 ቦታዎችን መምረጧል አስታወቀች፡፡


ከናይል ተፋሰስ ሃገሮች የምክክር ስብሰባዎች አንዱከናይል ተፋሰስሃገሮችየምክክርስብሰባዎች አንዱ
በዚህ ወር መጀመሪያ ደግሞ የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ሞርሲ በውኃ ደኅንነታቸው ላይ የሚፈጠርን “ማንኛውንም ሥጋት ለመያዝ ‘ሁሉም አማራጮች ክፍት’ ናቸው” ባሉ ጊዜ በውኃው አቅርቦት ላይ ያላቸውን ፍርሃት ጠቁመው እንደነበርና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በሰጡት ምላሽ የግብፅ መሪዎች “… ካላበዱ በቀር የጦርነትን አማራጭ ይወስዳሉ ብለን አናምንም …” ብለው ነበር፡፡

በናይል ሃገሮች መካከል የሰፋ ትብብር እንዲፈጠር የአሥር የተፋሰሱ ሃገሮች ሚኒስትሪዎችን መሪዎች የጁባ ስብሰባ በከፈቱ ጊዜ የደቡብ ሱዳን መንግሥት ተጠሪው ባርናባ ማሪያል ቤንጃሚን ጥሪ አሰምተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር አቶ አለማየሁ ተገኑም ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የጀመረችውን ግድብ ግንባታ ሥራ እንደማታቆም አስታውቀዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የማንንም ሃገር የመሻሻል ዕድል እንደማትቃወም የተናገሩት የግብፅ የውኃ ኃብቶች ምክትል ሚኒስትር አሕመድ ባህ ኤልዴይን ይሁን እንጂ ናይል ወንዝን በተመለከተ ማንኛቸውም ዕቅዶች ከመነደፋቸው በፊት መዘዞች ሁሉ ግምት ውስጥ ሊገቡ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

http://amharic.voanews.com

No comments:

Post a Comment