Monday, June 3, 2013

ወደውስጤ










ኤርሚያስ 18 ዓመቱ ነው፡፡ ቁመቱ 1፡85 ሲሆን ጸጉሩን ይፈርዘዋል የተገናኘነው ትምህርተ ቤት ግቢ ውስጥ ስለሆነ
ዩኒፎርም አርጓል ግን በራሱ ስታይል ነው ያሰፋው ሱሪው ስኪኒ ስታይል ነው ሰደሪያው ደግሞ በጣም አጭር ጥብቅ ያለች
ናት ከፖፕ አቀንቃኞች ክሪስን አብዝቶ ይወደዋል ኤርሚያስ ክሪስ ላይ የሚያያቸው አለባበስ ዳንስ በጠቅላላው ስታይሉ የኔ በሆነ
እኔ ባልኩት  እኔ ባረኩት እያለ በምኞት ዓለም ያልማል፡፡
እኔስ ብሆን ከእንደዚህ አይነት ምኞት የጸዳሁ ነኝ ማለት አልችልም  ማህበረሰቡ ጉዋደኞቼ ሚዲያው እንዲሁም የኔ ፍላጎት
ተጨምሮበት በብዙ ነገሮች ተጽኖ ስር የምወድቅበት ግዜ አለ፡፡ ማግኘት የምፈልገው ነገር እንኳ ብዙ ችግር እጄ ከገባ በኋላ
በመሰልቸት ወደ ሌላ መሻት እና ፍለጎት እገባለሁ፡፡ መቼም የውጭው ዓለም የሚፈጥትብኝ ተጽኖ ቀላል  አይደለም ማንነቴን እንድረሳ
ወደውስጤ እንዳላይ ራሴን እናዳልጠይቅ መልሱንም ከራሴ  እዳላገኝ የሚያረገኝ በዙ የፈተና ቀናት ነበሩብኝ እየወደኩ እየተናሳሁ እዚህ ደርሻለሁ፡፡
ጠይም ና የደስደስ ያላት ራሔል በምንም ይሁን በምን ገንዘብ አግኝታ አሪፍ የተባለውን ሞዴል መኪና ማሽከርከር  ጸዳ ያለ ቤት ውስጥ  መኖር  ፋሽን የሆኑ ልብሶችን መልበስና በቃ ሌላውን የሚስቀና ኑሮ መኖር የዘወተር ምኞቷ ነው ይህን ለማሳካት ደግሞ ወደ ባሀህር ማዶ ሔዳ ገንዘብ መሰብሰብ ትፈልጋለች ፡፡
ራሄል  ከጓደኞቿ ጋር   በብዛት በከተዋ ውስጥ አሉ በተባሉ ጭፈራቤቶች ደንበኛ ናት ከእነሱ ቃል አትወጣም  አንዳንዴ  ቤቷ ለማረፍ ፈልጋ ቢሆን እንኳ ከተጠራች የጓደኞቿን ግፊፉት መቋቋም ስለሚያቅታት ሳትወድ በግዷ ትወጣለች ራሄል የወደፊት ህለሟ ሞዴል መኪና መያዘዝ አሪፍ ቤት መስራት ና መዝናናትዋን መቀጠል ነው ጽኑ ምኞቷ ግን በአሁን እንቅስቃሴዋ ይህን ማድረግ ይቻላት ይሆን ? ወደራሳችን ለማየት እና ራሳችንን ለማዳመጥ እክል ከሚሆኑብን ነገሮች መሃከል ማህበረሰቡ ሃይማኖት ጓደኛ መገናኛ ብዙሃን እያልን መዘርዘር እንችላለን፡፡ 
ራሄል የኔ የምትለው ምን አላት  በውጭው ካየችውና ለማግኘት ከምትመኘው ውጪ ..ወደውስጧስ ለማሰብ ግዜ አላት …ሁልግዜ
በጓደኞቿ ቁጥጥር ስር ነች  የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ የሆነችው መስከረም ሃይሌ በእንዲህ አይነት ተጽኖ ስር ስንወድቅ
የኛ የምንለው ጥያቄ የኛ የምንለው መልስ  የኛ የምንለው ሀሳብ አይኖረንም የሌሎች ሃሳብ ሁሌም ትክክል ነው ብለን እናስባለን ትላለች፡፡


ወደራስ ማንነት ለማተኮር ብዙ ውጫዊ ግፊት ሊከሰትብን ይችላል ግፊቶችን መቋቋም ከቻልን ያኔ ራሳችንን በተገቢው መጠን
የማየት የመጠየቅ ና የመወሰን ሀይል ይኖረናል፡፡
ሚኪያስ ኮለል በሎ የሚፈስ  ድምጽ አለው  ርጋታው ከፊቱ ይነበባል፡፡
በርግጥ እኔ ስል ቀድሞ የሚመጣው ስሜ ነው ይላል ሚኪያስ ግን ማንነቴ  ከቁሳዊውም ነገር በላይ ነው ወደ ውስጥ ስመለከትና እራሴን ሳጤነው ህይወቴን የሚያንቀሳቅስ አንዳች ሃይል አለ ሲል ይጨምራል
ሚኪያስ ኮሌጅ እያለ መሆን በሚፈልገውና ማህበረስቡ የተየለየ ክብር በሚሰጠው ሙያ ምርጫ ላይ አጣበቂኝ ውስጥ ገብቶ እንደነበር ያስታውሳል ..ግን ወደራሱ በመመልከት…ራሱን በመጠየቅ  ሲችል የራሱ ባለቤት መሆን ችሏል  ህይወትን ቀለል አርጌ ነው የማየው ይላል ሚኪያስ
ከራሴ ጋር መነጋገሬ የሚፈጠሩብኝ ጥያቄዎችን መመለስ  ሌሎችን ለማክበርና ለማዳመጥ ምክንያት ሆኖኛል እንዲህ ልምድም አዳብረያለሁ   ሲል ይጨምራል
ልማድን መስበር ቀላል አይደለም  ውስጣችን ጥያቄ ሲፈጠር መልስን ከሌላ እንሻለን ይህ ነው እግዲህ በሌሎች ተጽእኖ ስር የሚያውለን  በእውነት እኔ ማኔ ነኝ   ልዩ የሆንኩበት ችሎታዪስ ምንድ ነው እንዴትስ ላወጣው እችላለሁ የሚሉና ሌሎች ብዙ ጥያቄዎች ሊፈጠሩብን ይችላሉ በርጋታና በጥሞና ካስተዋልነው  መልሱን እራሳችን ጋር ልናገኝው እንችላለን 
አንዳንዴ መስታወት ላይ ሆነን የማንን ምስል  ነው የምናስተውለው በርግጥ እኔ ነኝ ውይስ ሌላ   በሌላ ሃሳብ በሌሎች ተጽኖ በሌላ እውነታና ፍላጎት ተከብቤያለሁ እንደዛ ከሆነ የኔ የምለው ሓሳብ የኔ የምለው ኃይል የኔ የምለው ስብዕና ወዴት አለ
ራስን ለመሆን ራሰን ለማዳመጥ ራስን ለመጠየቅ እና ከራስ መልስ ለማግኘት ልምምድ ይጠቃል  ሰውነት በተመጣጠነ ምግብ እና ስፖርታዊ እንቀቅስቃሴ እንደሚገነባ ሁሉ ስብዕናም እንዲሁ በየግዜው ከራሳችን ጋር በምናደርገው ክትትል ሊገነባ ይችላል ትለናለች
የህይወት ክህሎት አሰልጣኟ መስከረም
·         እኔማነኝ
·         ምን መሆን እፈልጋልሁ
·         እኔ ላይ ተጽእኖ ያለው ማን ነው
·         ሳልፈልግ ለሰው ብዬ የማረገው ነገር አለ
·         በመንም መልኩ የማልደራደርባቸው እሴቶች አሉኝ
·         ለምስራው ስህት ኃላፊነቱን እወሰወዳለሁ
እነዚህን እና ሌሎችን ጥያቄዎች ማንሳት  የበለጠ ያለብንን ችግር ለመለየት እና ቀስ በቀስም ተገቢውን መልስ ለመስጠት ይረዳናል
በቀን ለተውሰነ ደቂቃ በጸጥታ ወደ ራሳችን የመመልከት ልማድን በማዳበር ወደስብዕናችን ልንመለስ እንችላለን ትላለች መስከለረም
 እኔ ሁልግዜ ምሽት ወደቤቴ መዳረሻ ከ 15-20ደቂቃ የእግር ጉዞ የማደረግ ልምድ አለኝ ይህ ምቹ ግዜዪ ነው ስለራሴ እጠይቃለሁ እመልሰላሁ …ውሎዪን እከልሳለሁ ያጎደልኩት አስተውላለሁ…አወጣለሁ አወርዳለሁ እጥላለሁ አነሳለሁ
ከዚህ ሁሉ ግን አትራፊ ነኝ ብዙ ግዜ ለጭንቀቴ ማስተንፈሻ ለጥያቄዎቼም መልስ የማገኝበት ልማዴ ነው….አንደገና በጥልቅ እተነፍሳለሁ ሌላ ጥያቄ ይፈጠራል ህይወት ሂደት ናታ፡፡

 



ሰለሞን ዮሃንሰ 

 የሬዲዮ ፕሮግራሙን ያድምጡ





No comments:

Post a Comment